የአየር ንብረት ለውጥ የቢሊዮኖችን ጤና አደጋ ውስጥ መጣሉ ተገለጸ
የኮፕ28 ጉባኤ የሰው ልጆች የመጨረሻ እድል ነውም ተብሏል
በሙቀት ምክንያት የሚሞቱ ዜጎች ቁጥር በሶስት እጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል
የአየር ንብረት ለውጥ የቢሊዮኖችን ጤና አደጋ ውስጥ መጣሉ ተገለጸ
የለንደን ዩንቨርሲቲ ባስጠናው ጥናት የአየር ንብረት ለውጥ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት አደጋ ውስጥ ማስገባቱን አስታውቋል፡፡
ጥናቱ የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ ከዓለማችን የተውጣጡ 52 ትናት እና ምርምር ተቋማት የተውጣጡ 114 ባለሙያዎች እንደተሳተፉበት ተገልጿል፡፡
እንደ ጥናቱ ከሆነ የሰው ልጅ ለአየር ንብረት ለውጥ ተገቢውን ትኩረት እየሰጠ አይደለም የተባለ ሲሆን የምድር ሙቀት በዚሁ ከቀጠለ በ2050 በሙቀት ምክንት የሚሞቱ ዜጎች ቁጥር በሶስት እጥፍ ይጨምራል ተብሏል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለማስቆም ኮፕ28 የመጨረሻው አማራጭ ነው የተባለ ሲሆን የተለያዩ እርምጃወፐችን መውሰድ የሚያስችሉ ውሳኔዎች እና ፖሊሲዎች ጸድቀው ሊተገበሩ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
የሰው ልጅ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እያደረገ ያለው ጥረት በቂ እንዳልሆነ ተገለጸ
ኪህ በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የተጀመሩ ስራዎች በፍጥነት ካልተጠናቀቁ የእስካሁኑ ጥረቶች ሁሉ ከመቆማቸው ባለፈ ዓለማችን የከፋ እና ታይቶ በማይታወቅ የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ልትመታ እንደምትችልም ተሰግቷል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር ይመክራል፡፡
ይህ ጉባኤ በተመድ አባል ሀገራት እየተዟዟረ በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በተባበሩት አረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡