የአረብ ኤምሬት ፕሬዝዳንት አል ናህያን ከሩሲያው አቻቸው ጋር ተወያዩ
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በሩሲያ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው
ፕሬዝዳንቱ የዩክሬንን ቀውስና ሌሎችን ግጭቶችን ለመፍታት ፖለቲካዊ መፍትሄዎችን በመውሰድ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጠንካራ አቋም መሆኑን አረጋግጠዋል
የአረብ ኤምሬት ፕሬዝዳንት አል ናህያን ከሩሲያው አቻቸው ጋር ተወያዩ።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ሀገራቸው የዩክሬንን ቀውስ ለመፍታትና ሰብዓዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ማንኛውንም ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
ሁኔታውን ለማረጋጋትና መረጋጋት ለመደገፍ "የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሁሌም ከጎን ናት" ሲሉ አሳስበዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት በሩሲያ እያረጉት ባለው የስራ ጉብኝት በሴንት ፒተርስበርግ በተደረገላቸው አቀባበል ወቅት ነው።
በዓለም ዙሪያ ሰላምና መቻቻልን ለመደገፍ ባደረጉ ጥረት "የሰላም ሰው" በመባል የሚታወቁት ፕሬዝዳንት አል ናህያን፤ የተራዘመውን ዩክሬንን ቀውስ ለመፍታት በዓለም ልብ ውስጥ ተስፋን ጭረዋል።
ፑቲን በዩክሬን ግጭት ውስጥ በርካታ ሰብዓዊ ጉዳዮችን ለመፍታት በተለይም የእስረኞችን መለዋወጥን በተመለከተ ፕሬዝዳንት አል ናህያን ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።
"በዩክሬን በተከሰቱት የእስረኞች ልውውጥ እና ሌሎች በርካታ ሰብዓዊ ጉዳዮችን ለመፍታት ላደረጋችሁት ጥረት ላመሰግናችሁ እወዳለሁ" ብለዋል።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በበኩላቸው በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ መድረኮች ላይ ሰላም እና
መረጋጋትን ለመደገፍ ሀገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።
የዩክሬንን ቀውስ ጨምሮ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን ለመፍታት ፖለቲካዊ መፍትሄዎችን በመውሰድ በማረጋጋት ፣ በመወያየት እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመደገፍ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጠንካራ አቋም መሆኑን አረጋግጠዋል።
የቀውሱን ሰብዓዊ ጉዳት ለመቅረፍ እና የእስረኞች ልውውጥን በሁለቱም ወገኖች የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።
መሪዎቹ በውይይታቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ስልታዊ አጋርነት በመገምገም ግንኙነቶች ለማጎልበት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።
አል ናህያን ሀገራቸው የትብብር ድልድዮችን በመገንባት ከሩሲያ እና ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ጋር የጋራ ጥቅሞችን በሚያጎለብት መልኩ አጋርነት ለመመስረት ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር "ዓለማችን ትረጋጋለች" ሲሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።