አረብ ኢምሬት በሽብርተኝነት ስትፈልገው የነበረውን ግለሰብ ከጆርዳን ተረከበች
ካላፍ አብደል ራህማን በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥሮ የ15 ዓመት እስር ውሳኔ ተላልፎበት ነበር
ግለሰቡ በአረብ ኢምሬት ያለውን አስተዳድር ከሙስሊም ብራዘርሁድ ጋር በመመሳጠር ድርጅት በመክፈት ወንጀል ክስ ቀርቦበት ነበር
አረብ ኢምሬት በሽብርተኝነት ስትፈልገው የነበረውን ግለሰብ ከጆርዳን ተረከበች።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ካላፍ አብደል ራህማን ሀሚድ አልሩማቲ የተሰኘን ግለሰብ በፈረንጆቹ 2013 ላይ በሽብርተኝነት ክስ ተከሶ በሌለበት የ15 ዓመት እስር ተላልፎበት ነበር።
ግለሰቡ በሀገሪቱ በሽብርተኝነት ከተፈረጀው ሙስሊም ወንድማማቾች ጋር የሚተባበር የሽብር ቡድን በማዋቀር የአረብ ኢምሬት አስተዳደርን ለመቃመም አሲሯል ተብሏል።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ከተመሰረተች ዛሬ 50 ዓመት ሞላት
እንደ ኢምሬት ዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ ይህ ግለሰብ በፈረንጆቹ 2013 ላይ በሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ15 ዓመት እስር ተላልፎበት ነበር።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ለጡረተኞች የመኖሪያ ፈቃድ እንደምትሰጥ ገለጸች
የጆርዳን አስተዳድር ይህን ተፈላጊ ወንጀለኛ በግዛቱ በህግ ቁጥጥር ስር ያዋለው ሲሆን ግለሰቡ ለአረብ ኢምሬት ተላልፎ መሰጠቱ ተገልጿል።
የአረብ ኢምሬት የሀገር ውስጥ ሚንስቴር ተፈላጊውን ወንጀለኛ ከጆርዳን መረከቡን አስታውቋል።
የአረብ ኢምሬት መንግሥት አክሎም ዜጎችን ከሽብር ጥቃት የመጠበቅ ግዴታውን ለመወጣት በሽብርተኞች እና ህገወጦች ላይ እርምጃ መውሰዱን እንደሚቀጥልም ገልጿል።