ከራዳር እይታ ውጪ የሚሆነው ድሮኑ የአየር ላይ የውጊያ ተልእኮዎችን በቀላሉ የመፈጸም አቅም አለው
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሷ አቅም የሰራቸውን የውጊያ ድሮን ይፋ አድርጋለች።
አረብ ኢሚሬትስ ድሮኑን ይፋ ያደረገቸው የአቡ ዳቢ እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የመከላከያ ኤግኢቢሽን (IDEX) ላይ መሆኑ ተነግሯል።
“ዘ ፌይሪ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የውጊያ ድሮን ለእይታ ሲቀርብም ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነም ነው የተገለፀው።
“ስውሩ” የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው የአረብ ኢሚሬትስ የውጊያ ድሮን ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ያሟላ እና ውጤታማ ተግባራትን መከወን የቻለ መሆኑም ነው የተነገረለት።
“ዘ ፌይሪ” የአረብ ኢሚሬትስ ድሮን 10.5 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤ 6.5 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ነው።
በጣም በከፍተኛ ፍጥነት የመፈትለክ አቅም ያለው ድሮኑ በሰዓት ከ1 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መጓዝ ይችላልም ተብሏል።
ድሮኑ ከውጊየ አላማ በተጨማሪም የተለያዩ የጦር መሳሪያ ጥይቶችን ለማጓጓዝም የሚውል ሲሆን፤ በአንድ ጊዜም 480 ኪሎ ግራም ድረስ ተሸክሞ መጓዝ ይችላል።
ምስጋና ለፍጥነቱ እና “ዘ ፌይሪ” ወይም ስውሩ ድሮን በቀላሉ በራዳር እይታ ውስጥ የማይገባ ሲሆን፤ ይህም ድሮኑ በቀላሉ የአየር ላይ የውጊያ ተልእኮዎችን እንዲፈጽም ያስችለዋል።
“ዘ ፌይሪ” ድሮን በአረብ ኢሚሬትስ ውስጥ በሚገኘው አቡዳቢ ኢንቨስትመንት ፎር አውቶኖመስ ስስተም (ADASI) ኩባያ ነው የተመረተው።
በድሮኑ ምርት ላይም የአረብ ኢሚሬትስ ባለሙያዎች እና ቴክኒሻኖች እንደተሳተፉበትም ነው የተነገረው።