አረብ ኢምሬትስ እና አሜሪካ የ100 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ተፈራረሙ
አረብ ኢምሬት እስከ 2035 ድረስ 100 ጊጋ ዋት ታዳሽ ሀይል ለማመንጨት ተስማምታለች
የአቡዳቢ ዓለም አቀፍ ፔተሮሊየም እና ትዕይንት እና ኮንፈረንስ በመካሄድ ላይ ይገኛል
አረብ ኢምሬት እና አሜሪካ የ100 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ተፈራረሙ፡፡
የተባበሩት አረብ ኢምሬት እና አሜሪካ እስከ ፈረንጆቹ 2035 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ 100 ጌጋ ዋት ታዳሽ ሀይል ለማመንጨት ከአሜሪካ ጋር ተስማምታለች፡፡
ስምነቱን የተባበሩት አረብ ኢምሬት ኢንዱስትሪ ሚኒስትር እና የአየር ንብረት ልዩ መልዕክተኛ ዶክተር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃቢር እና የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ልዩ አስተባባሪ አሞስ ሆችስቲን በአቡዳቢ ፈርመዋል፡፡
ስምምነቱን የአረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በስምምነቱ ፊርማ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙ ሲሆን ይህ ታዳሽ ሀይል አረብ ኢምሬት፣ አሜሪካ እና ሌሎች ሀገራት ለማምረት ተስማምታለች፡፡
በዚህ ስምምነት መሰረት አረብ ኢምሬት እየጨመረ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እና የሀይል ደህንነትን ለማስጠበቅ እንደምትሰራ ተገልጿል፡፡
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ከአሜሪካ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ከመሰረተች 50 ዓመት ያለፋት ሲሆን የዛሬውን ስምምነት ተከትሎ ሁለቱ ሀገራት በታዳሽ ሃይል ቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ በካርበን ሀይል ቅናሽ፣ በኑክሌር ሀይል ልማት እና በሌሎች ተያያዥ የሀይል ልማት ስራዎች ዙሪያ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
የአቡዳቢ ዓለም አቀፍ ፔተሮሊየም እና ትዕይንት እና ኮንፈረንስ በመካሄድ ላይ ሲሆን የጉባኤው ዓላማ የዓለማችንን የሀይል ፍላጎት ደህንነት ማስጠበቅ ነው ተብሏል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ የዓለም ሀይል ልማት ኩባንያ መሪዎች እና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን አስተማማኝ የሀይል አቅርቦት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ላይ ምክክሩ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ወይም ኮፕ27 ከቀናት በኋላ በግብጽ አስተናጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን የተባበሩት አረበብ ኢምሬት ደግሞ ኮፕ28 በሚቀጥለው ዓመት እንደታካሂድ ይጠበቃል፡፡