የአረብ ኢምሬትስ እና የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች በሁለት አመታት ውስጥ ለዘጠነኛ ጊዜ ሊገናኙ ነው
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ከዛሬ ጀምሮ በአሜሪካ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ
የፕሬዝደንቱ የአሜሪካ ጉብኝት ስልጣን ከያዙበት ከ2022 የወዲህ የመጀመሪያቸው ነው
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ሼህ ሞሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የአሜሪካ አቻቸው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ሊገናኙ ነው።
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ከዛሬ ጀምሮ በአሜሪካ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያካሄዱ ነው። የፕሬዝደንቱ የአሜሪካ ጉብኝት ስልጣን ከያዙበት ከ2022 የወዲህ የመጀመሪያቸው ነው።
መሪዎቹ የሚያደርጉት ስብሰባ በሁለት አመታት ውስጥ ለዘጠነኛ ጊዜ ሲሆን የአረብ ሀገር እና የአሜሪካ መሪዎች በዚህን ያህል ድግግሞች መገናኘታቸው በሪከርድነት ተመዝግቧል።
ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን እያደገ የመጣውን ግንኙነት እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያሳይ መሆኑም ተገልጿል።
አሜሪካ አረብ ኢምሬትስ እና አመራሯ ችግሮችን በመጋፈጥ እና በአለም ሰላም እና መረጋጋት እንዳፈጠር ለምታደርገው ጥረት በተደጋጋሚ አድናቆቷን ችራታለች።
ከዚህ በተጨማሪም የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ሼክ ሞሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በተለይ በቀጣናዊ ልማት፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመዋጋት እና በዘላቂ መፍትሄዎች ላይ ለተጫወቱት ሚናም አሜሪካ እውቅና ሰጥታቸዋለች።
መሪዎቹ በሚያደርጉት ስብሰባ ለ50 አመታት በዘለቀው የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኘነት እንዲሁም በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ እና በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ይመክራሉ ተብሏል።