የሙሴቬኒ ልጅ ለፕሬዝደንትነት የመወዳደር እቅዱን መተውን ገለጸ
አወዛጋቢ አስተያየቶችን በመስጠት የሚታወቀው ኬነሩጋባ አሁን ላይ የሀገሪቱ የጦር ኃላፊ ናቸው
ሀገሪቱን ለ38 አመታት የመሩት ሙሴቬኒ እስካሁን ለውድድሩ እጩነታቸውን ባያረጋግጡም፣ ለድጋሚ ምርጫ ይወዳደራሉ ተብሎ ይጠበቃል
የሙሴቬኒ ልጅ ለፕሬዝደንትነት የመወዳደር እቅዱን መተውን ገለጸ።
ኡጋንዳን ለረጅም ጊዜ የመሩት ፕሬዝደንት ዮሪ ሙሴቬኒ ልጅ በ2026 በሚካሄደው ምርጫ ለመወዳደር ይዞት የነበረውን እቅዱን መተውን በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
ሀገሪቱን ለ38 አመታት የመሩት ሙሴቬኒ እስካሁን ለውድድሩ እጩነታቸውን ባያረጋግጡም፣ ለድጋሚ ምርጫ ይወዳደራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
"በ2026 የምርጫ ወረቀት ላይ እንደማልኖር ላሳውቅ እወዳለሁ" ሲሉ ሙሆዚ ኬነሩጋባ በኤክስ ገጹ አስፍሯል።
"ለቀጣይ ምርጫ ፕሬዝደንት ሙሴቬኒን ሙሉ በሙሉ እደግፋለሁ" ያለው ሞሁዚ ደጋፊዎቹ ሙሴቬኒ ለሰባተኛ ዙር የስልጣን ዘመን እንዲያሸንፉ እንዲመርጣቸው ጠይቋል።
አወዛጋቢ አስተያየቶችን በመስጠት የሚታወቀው ኬነሩጋባ አሁን ላይ የሀገሪቱ የጦር ኃላፊ ሲሆን በመጨረሻ አባቱን ይተካል የሚል ሰፊ ግምት ተሰጥቶታል።
ሙሰቬኔ ልጃቸው በኤክስ ገጹ ኬንያን ለመውረር ካስፈራራ በኋላ በ2022 ሙሴቬኔ ኬንያን ይቅርታ ጠይቀዋል። የኡጋንዳ ተቃዋሚዎች ሙሴቬኒ በሀገሪቱ ዘውዳዊ ስርአት የመትከል ፍላጎት አላቸው የሚል ክስ አቅርበውባቸዋል።
ሙሴቬኒ ግን ይህን ክስ አስተባብለዋል።
ኡጋንዳን ከ1986 ጀምሮ የመሩት የ80 አመቱ ሙሴቪኒ የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ሁለት ጊዜ ህገመንግስት እንዲሻሻል አድርገዋል።
የፖፕ ሙዚቃ ኮከቡን ቦብ ዋይንን ጨምሮ የፖለቲካ ተቃዋሚዎቹ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሙሴቬኔ የጸጥታ ኃይሎችን ተቃዋሚዎችን ለማሰር፣ ለማስፈራራት ወይም ለማሰቃየት ይጠቀሙባቸዋል ሲሉ ይከሷቸዋል። ሙሴቬኒ እነዚህን ክሶች አይሸቀሉም።
በ2021 የተካሄደውን ምርጫ ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ዋይኔ የምርጫውን ውጤት አልተቀበለውም። ሙሴቪኒ ግን ምርጫው በጣም ፍትሃዊ የሚባል ነው ሲሉ ነበር የገለጹት።