ድርጊቱ የኡጋንዳን የስጋ ኢንዱስትሪ የሚጎዳ ሆኖ መገኘቱ ተገልጿል
በኡጋንዳ የጸረ ኤችአይቪ ኤድስ መድሃኒት ለአሳማ ይሰጥ እንደነበር ተገለጸ፡፡
የኡጋንዳው ማካራሪ ዩንቨርሲቲ ባደረገው ጥናት የጸረ ኤችአይቪ ኤድስ መድሃኒት አሳማ እና ዶሮ አርቢዎች ለእንስሳቱ እንደሚሰጡት አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
እንስሳት አርቢዎች የጸረ ኤችአይቪ ኤድስ መድሃኒቱን ለሚያደልቧቸው እንስሳት የሚሰጡት ቶሎ እንዲደልቡላቸው እና ለመሸጥ ዝግጁ እንዲሁኑላቸው ነው ተብሏል፡፡
የኡጋንዳ ብሔራዊ መድሀኒት ባለስልጣን የማካሬሪ ዩንቨርሲቲ የጥናት ግኝትን አምኖ ተቀብሏል የተባለ ሲሆን መረጃውን ግን ለህዝብ ይፋ እንዳላደረገ አስታውቋል፡፡
በባለስልጣኑ ከፍተኛ የመድሃኒት ተቆጣጣሪ አሞስ አቱማንያ ለሀገሪቱ ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ መድሃኒቱን አሳማ እና ዶር አርቢዎች ለምርታማነት ይረዳናል በሚል በፈረንጆቹ 2014 ላይ መጠቀማቸውን እንደሚያውቅ ገልጿል፡፡
የሰው ልጆች የጸረ ኤችአይቪ ኤድስ መድሃኒትን የወሰዱ እንስሳትን መመገብ ለጤና ከባድ ጉዳት እንደሚያመጣ የተናገሩት እኝህ የመድሃኒት ተቆጣጣሪ መረጃውን ለህዝብ ይፋ አለማድረጋቸውን አምነዋል፡፡
ኡጋንዳ "የሞቱ ምዕራባውያን" ልብስ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ እግድ ጣለች
ይሁንና የኡጋንዳ መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ስራው መድሃኒትን እንጂ ምግቦችን የመቆጣጠር ስልጣን አልተሰጠውም ሱሉ ለምክር ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በማካራሪ ዩንቨርሲቲ ጥናት መሰረት 50 በመቶ የአሳማ አርቢዎች እንዲሁም 25 በመቶ ዶሮ አርቢዎች የጸረ ኤችአይቪ ኤድስ መድሃኒቶትን ለእንስሳቶቻቸው ይሰጣሉ፡፡
ከኡጋንዳ ዋና ዋና የስጋ ገበያ ስፍራዎች የተወሰዱ ናሙናዎችም ይህን ጥናት ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ኡጋንዳ ስጋ እና እንስሳትን ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ ጥሩ ገቢ በማግኘት ላይ ስትሆን ይህ ርፖርት የውጭ ንግዷን እንዳይጎዳባት በሚል መረጃውን በወቅቱ ይፋ ከማድረግ ተቆጥባለች ተብሏል፡፡