ሶማሊላንድ ከሶማሊያ የተገነጠለችው በፈረንጆቹ በ1991 ቢሆንም የነጻ ሀገርነት አለምአቀፍ እውቅና አላገኘችም
ኡጋንድ ሶማሊያ እና ተገንጥላ ራሷን እያስተዳደረች ያለችው ሶማሊላንድ ውህደት እንዲፈጥሩ ለማድረግ እንደምታደራድር አስታውቃለች።
ሶማሊላንድ ከሶማሊያ ከተገነጠለች ሶስት አስርት አመታትን አስቆጥራለች።
የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዮሪ ሙሰቨኒ የማደራደሩን ሚና ለመወጣት የተስማማሙት ባለፈው አርብ የሶማሊላንድ ልዩ መልእክተኛ ጃማ ሙሳ ጃማ በኡጋንዳ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ መሆኑን የፕሬዝደንት ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
"ፕሬዝደንት ሙሰቨኒ በሶማሊላንድ እና ሶማሊያ መካከል ውህደት ለማመቻቸት ተስማምተዋል" ብሏል መግለጫው።
ሶማሊላንድ ከሶማሊያ የተገነጠለችው በፈረንጆቹ በ1991 ቢሆንም የነጻ ሀገርነት አለምአቀፍ እውቅና አላገኘችም።
ሙሰቨኒ እንደስትራቴጂ ሲታይ ስህተት ስለሆነ መገንጠልን አንደማይደግፉ ገልጸዋል።
ይህ ውህደት የአፍሪካ ቀንዷን ሶማሊያን የአልሸባብ ጥቃትን ጨምሮ በሌሎች ቡድኖች የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመቋቋም አቅም ይፈጥርላታል።