ፖለቲካ
የኡጋንዳው ፕሬዘዳንት ሙሰቨኒ በ58.64 በመቶ ድምጽ በድጋሚ ምርጫ አሸነፉ
በሮበርት ካያጉላኒ የሚመራው ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ 34.83 በመቶ ድምጽ አግኝቷል
በኡጋንዳ በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሙሰቨኒ ለ6ኛ ጊዜ ማሸነፋቸውን ምርጫ ኮሚሽኑ ይፋ አደረገ
የዩጋንዳ የወቅቱ ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ የአገሪቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ፍትህ ስምዖን ቢባባማ ሙሴቪኒ በፈረንጆቹ ጥር 14 ቀን በተካሄደው ምርጫ 58.64 ከመቶ ድምጽ በማግኘት አሸንፈዋል ብለዋል፡፡ ኮሚሽኑ የፕሬዘዳንት ሙሰቨኒን ማሸነፍ ቢገልጽም “ምርጫው ተጭበርብሯል” የሚሉ አስተያየቶች እየመጡ ነው ተብሏል፡፡
የሙሴቬኒ ዋነኛ ተፎካካሪ የሆኑት ሮበርት ካያጉላኒ ወይም በቅጽል ስማቸው ቦቢ ወይንም ከተዘረዘሩት ድምጾች 34.83 በመቶ አግኝተዋል፡፡
ሁለተኛ የወጣው የተፎካካሪ ፎረም ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ፓርቲ መሪ ፓትሪክ አሙራት ናቸው፡፡ አሙራት ከተጠቀሰው ድምፅ 3.24 በመቶውን ነው ያገኙት፡፡
በፈረንጆቹ 1986 ስልጣን የያዙት ሙሰቨኒ ስልጣናቸውን ለሌላ አምስት አመት ማራዘም ችለዋልለ፡፡ ለስድስተኛ ጊዜ ምርጫ ያሸነፉት የአሁኑ የኡጋንዳ ፕሬዘዳንት ዩዋሪ ሙሰቨኒ ኡጋንዳን ከፈረንጆቹ 1971-79 ድረስ ያስተዳደሩትን ኢዲ አሚን ከስልጣን ለማውረድ በተንቀሳቀሰው አማጺ ቡድን ውስጥ ሚና እንደነበራቸው ይነገራል፡፡