ኡጋንዳ የኮሮና ቫይረስ ወደ ህብረተሰብ ደረጃ ስለደረሰ አዳዲስ እርምጃዎችን እወስዳለሁ አለች
ኡጋንዳ የኮሮና ቫይረስ ወደ ህብረተሰብ ደረጃ ስለደረሰ አዳዲስ እርምጃዎችን እወስዳለሁ አለች
ኡጋንዳ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በህብረተሰብ መካከል መተላለፉ መጀመሩን ተከትሎ ስርጭቱን ለመግታት አዳዲስ እርምጃዎች እወስዳለሁ ስትል አስጠነቀቀች፡፡
አንደ ኡጋንዳ የኢንፎርሜሽን፣ኮሙኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጁዲዝ ናባኮባ ጤና ሚኒስቴር ጥብቅ እርምጃዎችን ይወስዳል ብለዋል፡፡
“የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወደ ህብረተሰብ ደረጃ ከፍ ብሏል፡፡ እዚህ ደረጃ ደርሷል ማለት ቫይረሱ በጣም ተስፋፍቷል ማለት ሲሆን በዚህ ደረጃ የአዳዲስ ተጠቂዎች መነሻ መፈለግ ከባድ ነው” ብለዋል ናባኮባ፡፡
ሚኒስትሩ እንዳሉት ከጤና ሚኒስቴር መመሪያ እኪመጣ ድረስ ሁሉም ሰው በቫይረሱ እንዳይያዝ መጠንቀቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት ወደ ህብረተሰብ በመውረዱ ጥንቃቄ ካልተደረጋ ሁሉንም ሰው መመርመር እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡
በኡጋንዳ የቫይረሱ ስርጭት አሁን እደረሰበት ደረጃ እንዳይደርስ በማዘግየት ሰባት ወራት ጠንካራ ስራ ስትሰራ መቆየቷን ሚኒስትር ናባኮባ ገልጸዋል፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ዮሪ ሙሰቨኒ ባለፈው እሁድ እንደተናገሩት የኮሮና ቫይረስ ከፍ ባለበት ሰአት ትምህርትቤቶች፣ የጸሎት ቤቶች፤የሀገሪቱ አለም አቀፍ በረራ አየርመንገዶችና ብሄራዊ ድንበሮቿን መከፈታቸውን አስታውቀው ነበር፡፡
በኡጋንዳ እስከ እሁድ ድረስ 7530 ሰዎች በኮሮና የተያዙ ሲሆን 3647 ሰዎች ደግሞ ማገገም ችለዋል፡፡ በሀገሪቱ እስካሁን 73 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡