በኡጋንዳ ባለፉት አምስት ወራት የምርጫ ጉዳዮችን የዘገቡ 16 ጋዜጠኞች ጥቃት ደርሶባቸዋል ተባለ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች በጸጥታ አካላት የሚፈጸመው ሃይል የተቀላቀለበት እርምጃ ልጓም እንዲበጅለትና በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በመብት አንቂዎች ላይ የቀረበው ክስ እንዲሰረዝ ኡጋንዳን አሳስበዋል፡፡
የፖፕ ንጉስ የሆነው ቦቢ ዋይኔ በፈረንጆቹ ጥር 14 ለተቀጠረው የኡጋንዳ ምርጫ ጠንካራ የፕሬዘዳንት ሙሰቨኒ ተቀናቃኝ ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡ ባለፈው እሁድ ዋይን ወይም በትክክለኛ ስሙ ሮበርት ኪያጉላኒ የዋይን ኮንቮይ ቁስለኛ ጋዜጠኛ ለህክምና እርዳታ እያጓጓዘ ባለበት ሰአት አንደኛው የግል ጠባቂው መገደሉን ተናግሯል፡፡
“ከምርጫ ጋር የተያያዘው ሁከት፣የፖሊሶችና ሀይል የተቀላቀለበት እርምጃ እንዲሁም በሰላማዊ ሰልፈኞች፣ በፖለቲካና በሲቪል ማህበረሰብ ላይ እየደረሰ ያለው ወከባ በጣም ያሳስበናል”ብለዋል የተመድ ባለሙያዎች ባወጡት መግለጫ ፡፡
ሮይተርስ የፕሬዘዳንቱና የመንግስት ቃልአቀባዮችን የጠየቀ ቢሆንም በጉዳዩ ላይ ምላሽ አለማግኘቱን ገልጿል፡፡ ዋይን እያካሄደ ባለው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ድጋፍ እያገኘ ሲመጣ የጸጥታ ሃይሎች እርምጃ ማየሉን አስታውቋል፡፡
ባለፈው ህዳር የዋይንን መታሰር ተከትሎ በተፈጠረ አመጽ በትንሹ 54 መገደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ፖሊስ በጊዜው ወደ 600 የሚጠጉ ሰዎችን ማሰሩን አስታውቆ ነበር፣መንግስትም በጊዜው አመጽና ዝርፊያን ለማስቆም ወታደር መላኩን አስተውቆ ነበር፡፡
ባለፉት አምስት ወራት የምርጫ ጉዳዮችን የዘገቡ 16 ጋዜጠኞች ጥቃት እንደደረሳባቸው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡