ብሪታኒያ የኮሮና ታማሚዎችን ወደ ሆቴሎች ልታዛውር ነው
ቫይረሱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰበት የሚያዝያ ወር ከነበረው 55 በመቶ በላይ ታማሚዎች በሆስፒታሎች ይገኛሉ
ታማሚዎች ወደ ሆቴል የሚዛወሩት ሆስፒታሎች በከፍተኛ መጠን በመጨናነቃቸው ነው ተብሏል
በብሪታኒያ በአሁኑ ወቅት ከ 35,000 በላይ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች በተለያዩ ሆስፒታሎች ውስጥ እንደሚገኙ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡ የጤና ሚኒስትሩ ማት ሀንኮክ እንዳሉት የሆስፒታሎችን መጨናነቅ ለመቅረፍ ታማሚዎቹን ወደ ሆቴሎች ለማዛወር ታቅዷል፡፡ ከፍተኛ ህክምና ከሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች ውጭ ያሉት ናቸው ወደ ሆቴሎች የሚዛወሩት፡፡
በቅርቡ አዲስ የኮሮና ዝርያ የተገኘባት ብሪታኒያ ፣ የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ደረጃ ካጠቃቸው እና እየተዛመተባቸው ካሉ ሀገሮች አንዷ ነች፡፡ ቫይረሱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰበት የሚያዝያ ወር ከነበረው ከ55 በመቶ በላይ ታማሚዎችን ሆስፒታሎች እያስተናገዱ እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡