ከ12 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊያን በተፈናቀሉበት በዚህ ጦርነት ሩሲያ ዋነኛዋ ስደተኛ ተቀባይ ሀገር ሆናለች
500 ቀናት የሞላው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት
ለአንድ ሳምንት ለልዩ ዘመቻ በሚል የተጀመረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት 500ኛ ቀኑን ሞልቷል።
እንደ ተመድ የስደተኞች ሎሚሽን መረጃ ከሆነ ከ12 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊያን ከቤታቸው ተፈናቅለዋል።
ዩክሬን በደረሰባት ውድመት ምክንያት ከ400 ቢሊዮን በላይ ዶላር ያስፈልጋታል ተብሏል።
ጦርነቱ አሁን በመልሶ ማጥቃት መልኩ የቀጠለ ሲሆን የሟቾች እና የተፈናቃዮችም ቁጥር እንደሚጨምር ይጠበቃል።