ፖለቲካ
የቻይናው ዢ ጂንፒንግ ፑቲን በዩክሬን የኒውክሌር ጥቃትን እንዳይፈጽሙ አስጠነቀቁ
የቻይና ባለስልጣናት የሩሲያ መሪ የአቶሚክ ዛቻ እንዲገቱ ማሳመናቸውን እውቅና ሰጡ
ቤጂንግ በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ላይ ስጋት አንጸባርቃለች
የቻይናው ዢ ጂንፒንግ ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳይጠቀሙ አስጠንቅቀዋል። ይህም ቤጂንግ በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ስጋት እንዳላት የሚያመለክት ነው ተብሏል።
ምንም እንኳን ቤጂንግ ለሞስኮ "ድብቅ ድጋፍ" እንደምትሰጥ በምዕራቡ ዓለም ወቀሳ ቢቀርብባትም የጦርነቱ ጦስ እንዳሳሰባት ተነግሯል።
መልእዕቱ የተላለፈው የቻይናው ፕሬዝዳንት በመጋቢት ወር በሞስኮ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ነው ተብሏል።
የቻይና ባለስልጣናት የሩስያ ፕሬዝዳንት በዩክሬን ላይ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመጠቀም ከሰነዘሩት ዛቻ እንዲመለሱ በማሳመን በግል እውቅና መስጠታቸውን ተናግረዋል።
ፋይናንሻል ታይምስ እንደዘገበው የቻይና መንግስት ከአውሮፓ ጋር ያለውን "የተበላሸ" ግንኙነት ለመጠገን ፑቲንን እንዲህ አይነት መሳሪያ እንዳይጠቀሙ መከልከል የዘመቻው ማዕከል አድርገዋል።
ቻይና ሞስኮ በዩክሬን ላይ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን እንዳትጠቀም በተደጋጋሚ በአደባባይ ተቃውማለች ሲል ዘገባው ጠቅሷል።
ነገር ግን የኪየቭ ደጋፊዎች የቤጂንግን ቁርጠኝነት ከሀገራቱን "ገደብ የለሽ" አጋርነት ጋር በእጅጉ የሚጣረስ ነው ባይ ናቸው።