ሙሳ ፋኪ ለዘሌንስኪ “ግጭቱን ለማስቆም አስቸኳይ ውይይት አስፋለጊ ነው” የሚለው የህብረቱ አቋም መሆኑን መግለጻቸውን ተናግረዋል
ሙሳ ፋኪ ለዘሌንስኪ “ግጭቱን ለማስቆም አስቸኳይ ውይይት አስፋለጊ ነው” የሚለው የህብረቱ አቋም መሆኑን መግለጻቸውን ተናግረዋል
ዘሌንስኪ የ”በአፍሪካ ህብረት ንግግር ማድረግ እፈላጋለሁ” ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸው አይዘነጋም
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ በዛሬው እለት በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ንግግር ማድረጋቸውን የአፍሪካ ህብረት አስታወቀ፡፡
የአፍሪካ ህብረት የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ያቀረቡትን የ”በአፍሪካ ህብረት ንግግር ማድረግ እፈላጋለሁ” ጥያቄ መቀበሉ ከሁለት ሳምንት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት ዘሌንስኪ በዛሬው እለት በህብረቱ ጉባኤ ላይ በበይነ መረብ ንግግር ማድረጋቸው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበሩ ሙሳ ፋኪ ማሃመት አስታውቀዋል፡፡
ሊቀ መንበሩ በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ ከዘሌንስኪ ጋር በነበራቸው ቆይታ “የዓለም ሰላም ለመመለስም ሆነ ግጭቱን ለማስቆም አስቸኳይ ውይይት ያስፈልጋል የሚለውን የአፍሪካ ህብረት አቋም ገልጸናል” የሚል ጥቅል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ከአሁን ቀደም በተለያዩ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ምክር ቤቶች የበይነ መረብ ንግግሮችን አድርገዋል፡፡
ኬንያን መሰል አንዳንድ የአፍሪካ ህብረት አባል ሃገራት ሩሲያ በዩክሬን ጦሯን ማዝመቷን በይፋ ቢቃወሙም ብዙዎቹ ግን እስካሁን አቋማቸውን በአደባባይ አላንጸባረቁም፡፡
ጦርነቱ እንዲቆምና ሰላማዊ መፍትሄዎች እንዲፈለጉ ከመጠየቅም ውጪ በገሃድ ሩሲያን አውግዞ እርምጃዎችን የወሰደ ሀገርም የለም፤ ምንም እንኳን አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን አጥብቀው የሚፈልጉት ጉዳይ ቢሆንም፡፡
በዛሬው እለት በአፍሪካ ህብረት ንግግር ያደረጉት ዘሌንስኪም ለአባል ሃገራቱ መሪዎች ስለ ጦርነቱ በመግለጽ የሃገራቱን አቋም ለማወቅና ድጋፍ ለማሰባበስብ በሚል መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡