የዩክሬን ጦር በሁሉም የመልሶ ማጥቃት አቅጣጫዎች እየገሰገሰ ነው ተባለ
የዩክሬን ወታደሮች በጦርነት ጉዳት በደረሰባት ምስራቃዊ የባክሙት ከተማ ዙሪያ እየተንቀሳቀሱ ተብሏል
ሩሲያ የኪየቭን ግኝት በማጣጣል ጦሯ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት ነው ብላለች
የዩክሬን ወታደሮች በሩስያ ጦር ላይ ባደረጉት የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ በሁሉም አቅጣጫ እየገፉ መሆናቸውን የመከላከያ ባለስልጣናት ተናገሩ።
በዚህ ወር የመልሶ ማጥቃት ዘመቻው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ዩክሬን በደቡብ ምስራቅ የሚገኙ መንደሮችን መቆጣጠሯንም ገልጸዋል። ምንም እንኳን ሩሲያ አሁንም በምስራቅ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ "ይዞታወቿ" ላይ ብትሆንም።
ምክትል የመከላከያ ሚንስትር ሃና ማሊያር "ስለ አጠቃላይ ግንባሩ ካወራን በምስራቅ እና ደቡብ ስልታዊ ተነሳሽነትን ይዘን በሁሉም አቅጣጫ እየገሰገሰን ነው" ብለዋል።
ሮይተርስ በጦር ሜዳ ላይ ያለውን ሁኔታ ማረጋገጥ አልቻሉም ብሏል።
እ.አ.አ. በየካቲት 2022 "ልዩ ተልዕኮ" በሚል ዩክሬን ላይ ዘመቻ የጀመረችው ሩሲያ የኪየቭን ግኝት አልተቀበለችውም። ሞስኮ የዩክሬን ጦር ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው ስትል ተናግራለች።
ማሊያር እንደተናገሩት የዩክሬን ወታደሮች በጦርነት ጉዳት በደረሰባት ምስራቃዊ የባክሙት ከተማ ዙሪያ "በታማኝነት" እየተንቀሳቀሱ ነው። ይህም በሩሲያ ወታደሮች የተያዘ ሲሆን ዋናው ውጊያ በከተማዋ ዙሪያ እየተካሄደ ነው ብለዋል።
መከላከያ ሚንስትሯ የመልሶ ማጥቃቱ ውጤታማነት መገምገም ያለበት "በተለያዩ ወታደራዊ ተግባራት" እንጂ በግስጋሴና አካባቢን ነጻ ማውጣት ብቻ እንዳልሆነ ተናግረዋል ።