ስድስት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ወደ ሩሲያ እና ዩክሬን ሊያቀኑ ነው
መሪዎቹ ወደ ሞስኮ እና ኪቭ የሚያቀኑት ለሩሲያ-ዩክሬን ሰላም ፍለጋ ነው ተብሏል
መሪዎቹ ጦርነቱን ሊያቆም የሚችል ውይይት እንዲደረግ የሁለቱን ሀገራት ፕሬዝዳንቶች ማሳመን ይፈልጋሉ ተብሏል
ስድስት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ወደ ሩሲያ እና ዩክሬን ሊያቀኑ ነው፡፡
ስድስት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ለሰላም ተልዕኮ ወደ ፖላንድ እንደሚጓዙ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ተናገሩ።
ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የአፍሪካ መሪዎች ቡድን በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ለሽምግልና ወደ ፖላንድ ያቀናሉ ብለዋል።
"ሐሙስ ከእነሱ ጋር መጓዝ ነበረብኝ። አሁን በኮሮና ቫይረስ በመያዜ ምክንያት ቡድኑን መቀላቀል እንደማልችል ይፋዊ መልዕክት ልኬያለሁ" ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።
አያይዘውም ከኮሞሮስ፣ ግብጽ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሴኔጋል፣ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ዛምቢያ የተውጣጡ ስድስት የአፍሪካ ፕሬዝዳንቶች ሩሲያ እና ዩክሬንን ለማሸማገል ወደ ኪየቭ በባቡር ይጓዛሉ።
አሜሪካ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከሩሲያ ጋር መደራደር እንደምትፈልግ ገለጸች
የአፍሪካ መሪዎች የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነትን ሊያቆም የሚችል ውይይት እንዲደረግ ማሳመን ይፈልጋሉ ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ በኮሮና ቫይረስ በመያዛቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሩሃካና ሩዋንዳን እንዲወክሉ ፈቅደውላቸዋል ተብሏል።
ባለፈው ሳምንት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ተነጋግረው ስለ አፍሪካ መሪዎች "የሰላም ተልዕኮ" ገለጻ እንዳደረጉ ተነግሯል።
"ፕሬዚዳንት ፑቲን የአፍሪካ መሪዎችን ተነሳሽነት በደስታ ተቀብለዋል። የሰላም ተልዕኮውን ለመቀበል ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል" ሲል የራማፎሳ ጽህፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ገልጿል።
በመግለጫው ላይ ሙሴቬኒ የአፍሪካ መሪዎች "በተጨማሪም ሩሲያውያንን ለማግኘት ወደ ሩሲያ ይሄዳሉ" በማለት ተልዕኮአቸውን እንዲሳካላቸው ተመኝተዋል።