ፖለቲካ
ሩሲያ፣ በዩክሬን ምዕራባዊ ግዛት "ወሳኝ መሰረተ ልማት" መምታቷ ተገለጸ
ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭ እና ሌሎች ከተሞች ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት አደረሰች
ይህ ጥቃት ዩክሬን በሩሲያ የተያዙ ቦታዎችን ለማስለቀቅ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ከከፈተች ወዲህ በቅርብ የተፈጸመ የአየር ጥቃት ነው
ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭ እና ሌሎች ከተሞች ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት አደረሰች
ሩሲያ፣ በኪቭ እና በምዕራብ ዩክሬን በምትገኘው ልቪቭ ከተማ ወታደራዊ እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ማድረሷን የዩክሬን ባለስልጠናት ተናግረዋል።
ከሩሲያ ብሪያንስ ግዛት እና ከአዞቭ ባህር የየተተኮሱ ኢራን ሰራሽ የሆኑትን ሸሀድ ሚሳይሎችን መትታ መጣሏን ዩክሬን ገልጻለች።
ዩክሬን ከተተኮሱት 35 ሚሳይሎች 32ቱን መትታ መጣሏን ብትገልጽም በልቪቭ የሚገኘው ወሳኝ መሰረተ ልማት መመታቱን ገልጻለች።
የልቪቭ ግዛት አስተዳዳሪ ምክስይም ኮዚትስኪይ የተመታው መሰረተ ልማት ከግንባር 70 ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።
አስተዳዳሪው በጥቃቱ የተመታው መሠረተ ልማት ምን እንደሆነ ገልጽ አላደረጉም።
ይህ ጥቃት ዩክሬን በሩሲያ የተያዙ ቦታዎችን ለማስለቀቅ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ከከፈተች ወዲህ በቅርብ የተፈጸመ የአየር ጥቃት ነው።
ዩክሬን በመልሶ ማጥቃት ዘመቻው 113 ስኩየር ኪሎሜትር ስፋት ያለው ቦታ ከሩሲያ ማስለቀቋን መግለጿ ይታወሳል።
ነገርግን ሩሲያ ዩክሬን አስለቀቅሁ ያለችውን ቦታ መልሳ መያዟን ገልጻለች።