ፖለቲካ
በናጎርኖ ካራባህ ግዛት ግጭት እንዲቆም የተመድ ዋና ጸኃፊ አሳሰበ
ግጭቱ የተቀሰቀሰው አዘርባጃን በትናንትናው እለት በግዛቷ ውስጥ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ ነው

የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በናጎርኖ ካራባህ ግዛት እንደአዲስ የተቀሰቀሰው ግጭት በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስበዋል
የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በናጎርኖ ካራባህ ግዛት እንደአዲስ የተቀሰቀሰው ግጭት በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስበዋል።
ግጭቱ የተቀሰቀሰው አዘርባጃን በትናንትናው እለት በግዛቷ ውስጥ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ ነው።
ግጭቱን በጽኑ ያወገዙት ዋና ጸሀፊው ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም እና በፈረንጆቹ 2020 የተፈረመው ተኩስ አቁም እና አለምአቀፋ የሰብአዊነት ህግ በጥብቅ ሊከበር ይገባል ብለዋል።
የአዘርባጃን የመከላከያ ሚኒስቴር በግዛቷ እየወሰደው ያለው እርምጃ ስኬታ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል
ሚኒስቴሩ "የየአርመኒያ ጦር የሆኑ የውጊያ ቦታዎች፣ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች፣ የጸረ- አውሮፕላን መከላከያ መሳሪያዎች፣ የሬድዮ ኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር ጣቢያዎች እና ሌሎች ወታደራዊ መሳሪያዎች ተደምስሰዋል" ብሏል።
አዘርባጃን በአርመንያ ቀጥጥር ስር በምትገኘው ግዛት ላይ ወታደራዊ ዘመቻ በመክፈት ተገንጥላ ያለችውን ግዛት ለማንበርከክ ጥረት እያደረገች ነው።
የግዛቷ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት አዘርባጃን በከፈተችው ጥቃት ሰባት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እና 20 ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጿል።