የተመድ የሰብአዊ ጉዳይ ማስተባበሪያ ቢሮ ስድስት የእርዳታ ሰራተኞች በሶማሊያ፣ በደቡብ ሱዳንና በሶሪያ መገደላቸውን አስታውቋል
የተመድ የሰብአዊ ጉዳይ ማስተባበሪያ ቢሮ ስድስት የእርዳታ ሰራተኞች በሶማሊያ፣ በደቡብ ሱዳንና በሶሪያ መገደላቸውን አስታውቋል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የእርዳታ ባለስልጣን በተለያዩ የአለም ክፍል በእርዳታ ሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አውግዟል፤ የሰብአዊ ሰራተኞችን ኢላማ አድርገው ያጠቁም ወደ ህግ መቅረብ አለባቸው ብለዋል፡፡
እንደ ተመድ የሰብአዊ ጉዳይ ማስተባበሪያ ቢሮ ስድስት የእርዳታ ሰራተኞች በሶማሊያ በደቡብ ሱዳንና በሶሪያ ተገድለዋል፡፡ በደቡብ ሱዳን የተገደሉት ሁለት የእርዳታ ሰራተኞች በጎርፍ የተጎዱና በግጭት የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳታ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ነበር፡፡ በሶማሊያ ወሳኝ ህክምና በሆነው የፖሊዮ ክትባት ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች መገደላቸውንም ቢሮው ገልጿል፡፡
ተመድ ሁለት የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች በሰሜን ምእራብ ሶሪያ ለህጻናት ተስማሚ ወደሆነ ቦታ በመንቀሳቀስ ላይ ሳሉ ተገድለዋል፡፡
የተመድ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርክ ሎውኮክ በሰጡት መግለጫ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው የሰብአዊነት ስራ በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ የተቃጣ ነው ብለዋል፡፡
አስተባባሪው“ይህን ግፍ የፈጸሙ ወደ ህግ መቅረብ አለባቸው፤ መንግስት መመርመርና መክሰስ አለበት፡፡ የአለምአቀፍ ህግ መከበር አለበት” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በፈረንጆቹ 2019 በእርዳታ ሰራተኞች ላይ የደረሰው ግድያ ከሁሉም ያለፉት አመታት እንደሚበልጥ የሰብአዊ ሰራተኞች መረጃ ያመለክታል፡፡ እንደመረጃው ከሆነ 125 የእርዳታ ሰራተኞች ተገድለዋል፡፡