ከሁለት አስርት አመታት በላይ ሲፈለጉ የነበሩት የ87አመቱ ግለሰብ ግንቦት ወር በፈረንሳይ መያዛቸው ይታወሳል
ከሁለት አስርት አመታት በላይ ሲፈለጉ የነበሩት የ87አመቱ ግለሰብ ግንቦት ወር በፈረንሳይ መያዛቸው ይታወሳል
የሩዋንዳው የዘር ማጥፋት ተጠርጣሪ ፍሊሲን ካቡጋ በታንዛኒያ ለሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ችሎት ሊሰጥ እንደሚችልና ተጠርጣሪው በፈረንሳይ እንዲዳኝ ያቀረበውን መከራከሪያ ወደ ጎን በመተው የፈረንሳይ ፍርድቤት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
የተመድ አቃቤ ህግ የቀድሞውን የሻይና ቡና ባለሀብት ለሁቱ ሚልሻዎች የገንዘብ ድጋፍ በማድረግና ብዙ ቁጥር ያላቸውን ጎራዴዎች ከውጭ በማስገባት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቱሲዎች በፈረንጆቹ 1994 በ100 ቀናት ውስጥ እንዲጨፈጨፉ አድርገዋል ብሎ ከሷቸዋል፡፡
ከሁለት አስርት አመታት በላይ ሲፈለጉ የነበሩት የ87አመቱ ግለሰብ ባለፈው ግንቦት ወር በፈረንሳይ መያዛች ይታወሳል፡፡
ተጠርጣሪው ካቡጋ ክሱን አስተባብለዋል፤ ዘርማጥፋት ፈጸመዋል የሚለውን በዚህ ወንጀል መከሰሳቸው ውሽት ነው ብለዋል፡፡
የፈረንሳይ ፍርድ ቤት ባወጣው መግለጫ ተጠርጣሪውን ወደ ተመድ የታንዛኒያ ፍርድ ቤት ሲዛወር ምንም የህግና የጤና መሰናክሎች እንዳይኖሩ ምርመራ ቡድኑ ከግምት አስገብቷል፡፡
የካቡጋ ጠበቃ ግን የተጠርጣሪው ጤና አሳሳቢ ነው፤በተለይ በዚህ በኮሮና ወቅት ወደ ታንዛኒያ መሄድ አደገኛ ነው ብለዋል፡፡
ጠበቃው አለምአቀፍ የመያዝ ፍቃድን በአግባቡ ባለመፈተሸ ህግ መንግስት ጥሷል ብለው ይከራከራሉ፡፡
ነገርግን የፈረንሳይ ይግባኝ ሰሚ ችሎት የታችኛው ፍርድቤት በፈረንጆቹ ሰኔ 3 ካቡጋ ተላልፎ እንዲሰጥ ያስተላለፈውን ውሳኔ አጽቋል፡፡