ሳይንቲስቶች ይህ ያልተለመደ ዝናብ የተባባሰው በአየርንብረት ለውጥ ምክንያት ነው ብለዋል
ሳይንቲስቶች ይህ ያልተለመደ ዝናብ የተባባሰው በአየርንብረት ለውጥ ምክንያት ነው ብለዋል
ለወራት በቆየው ከባድ ዝናብ የናይል ወንዝ ሞልቶ በመፍሰሱ ምክንያት በደቡብ ሱዳን ቀጥራቸው ከ600ሺ የሚበልጡ ሰዎች ከሀምሌ ጀምሮ ከቤታቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) አስታውቋል፡፡
በድህነት ውስጥ የምትኖረው የምራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ከሳለፈችው የአምስት አመት የእርስበእርስ ጦርነት ገና ያልተላቀቀችና በምግብ እጥረት የምትሰቃይ ነች፡፡ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ ይህ ያልተለመደ ዝናብ የተባባሰው በአየርንብረት ለውጥ ምክንያት ነው፡፡
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ጎርፍ የመከላከል ስራውን ማወሳሰቡን ተመድ የገለጸ ሲሆን እርዳታ የማድረስ ወጭም እየጨመረ መሄዱንም አስታውቋል፡፡
ተመድ ለጎርፍ ተጎጅዎች 10 ሚሊዮን ዶላር የመደበ ሲሆን በአመቱ መጨረሻ 40 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ከሩዋንዳው የዘር ፍጅት ቀጥሎ 12ሚሊዮን ህዝብ ተፈናቀለበት ክስተት የደቡብ ሰዱኑ የእርስበእረስ ግጭት ነው፡፡