78ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው እለት ተጀምሯል
የአለም ወቅታዊ ፈተና እና ቀጣይ መፍትሄዎችን በተመለከተ የሀገራት መሪዎች በየአመቱ መስከረም ወር ላይ የሚመክሩበት የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በኒውዮርክ ተጀምሯል።
78ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ምድራችን እየፈተኑ የሚገኙ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ላይ ከ150 በላይ የሀገራት መሪዎች ይመክሩበታል።
በመንግስታቱ ድርጅት ማቋቋሚያ ቻርተር መሰረት በፈረንጆቹ 1945 የተጀመረው የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የሀገራት መሪዎች በ15 ደቂቃ ውስጥ መልዕክታቸውን የሚያስተላልፉበት ነው።
በፈረንጆቹ 1960 በጠቅላላ ጉባኤው ንግግር ያደረጉት የወቅቱ የኩባው መሪ ፊደል ካስትሮ 4 ስአት ከ30 የሚወስድ ረጅም ንግግር በማድረግ ክብረወሰን ይዘዋል።
193 የተመድ አባል ሀገራት እና ታዛቢዎች የሚሳተፉበት ጉባኤ እውነታዎችን ይመልከቱ፦