ሩሲያ በዩክሬን ባካሄደችው “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” የተበሳጩት ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ማእቀብ ሁሉ በመጣል ላይ ናቸው
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ እግዱን የጣለው ሩሲያ በዩክሬን ባካሄደችው “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ወታደሮቿ መጠነ ሰፊ እና ስልታዊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል የሚሉ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ይህ ወሳኔ የተላለፈው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ ነው፡፡
በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ግልጽ ጦርነት የተጀመረ ሲሆን፤ ከ3 ሚሊየን በላይ ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደዳቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በሪፖርት ገልጿል።
ሩሲያ ጎረቤቷ ዩክሬን ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከፈረንጆች የካቲት 24፣ 2022 ጀምሮ ወታደራዊ ዘመቻ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ መጀመሯ ይታወቃል።
የዩክሬን ሃይሎች ጠንካራ ተቃውሟቸውን የፈጠሩ ሲሆን ምዕራባውያን ሩሲያ ኃይሏን እንድታስወጣ ከፍተኛ ማዕቀብ ጥለዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯን የሚያወግዘዉን የዉሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት የከፈተችው፣የኔቶ ጦር ዩክሬንን ጨምሮ ወደ ቀድሞ የሶቬት ህብረት ሀገራት እተሰፋፋ ነው፤ይህም ለደህንነቷ አስጊ እንደሚሆን በመግለጽ ነበር።የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እደቀጠለ ቢሆንም ሀገራቱ ችግሩን ለመፍታት ውይይታቸውን ጀምረዋል።