ተመድ የአፍሪካ የበረዶ ግግሮች ሊቀልጡ እንደሚችሉና ሚሊዮኖችን ለድርቅ ሊዳርጉ እንደሚችሉ ገለጸ
በፈረንጆቹ 2020 የአፍሪካ አማካይ የሙቀት መጠኑ በ 0.86 ዲግሪ ሴልሺየስ ከፍ ያለና የአፍሪካ ሦስተኛው ሞቃታማ ዓመት ነበር ተብሏል
የታንዛንያው ክሊማንጃሮ፣ የኬንያው ኬንያ ተራራ እና የኡጋንዳው ርዌንዞሪስ እንደፈረንጆቹ በ2040 ሊጠፉ ይችላሉ ተብሏል
አፍሪካ ውስጥ የሚገኙትና የሚደነቁት የምስራቃዊ ግግር በረዶዎች በየሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ የሚጠፉ በመሆናቸው ሚልዮኖች ለአደጋ ሊጋለጡ እንደሚችሉ ተመድ አስጠነቀቀ፡፡
የተመድ የአየር ንብርት ኤጀንሲ በአሁኑ ወቅት አፍሪካ ግግር በረዶዎች ሊቀልጡ እንደሚችሉና 118 ሚልዮን የሚሆኑ አፍሪካውያን ለድርቅ፣ጎርፍ፣ከፍተኛ ሙቀት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሊጋለጡ እንደሚችሉ እንዲሁም እስከ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ከአህጉራዊው የሀገር ውስጥ ምርት 3% ቅናሽ እንደሚያስከትል ገልጿል፡፡
በቅርቡ የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ከአፍሪካ ህብረት ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር ያወጡት ሪፖርትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከሚመጣው የአየር ሁኔታ አደጋ ጋር አህጉሪቱ ከፍተኛ አደጋ እንደተጋረጠባት ማመልቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በፈረንጆቹ 2020 የአፍሪካ አማካይ የሙቀት መጠኑ በ 0.86 ዲግሪ ሴልሺየስ ከፍ ያለና የአፍሪካ ሦስተኛው ሞቃታማ ዓመት ነበር ተብሏል፡፡
ሙቀቱ በዝግታ ያደገ ቢሆንም ተፅእኖው አሁንም አጥፊ ነው ትበለዋል፡፡ከከፍተኛው ሞቃታማ ቀጠናዎች ይልቅ በዝግታ ሞቅቷል፣ ግን ተፅእኖው አሁንም አጥፊ ነው።
የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ዋና ጸሃፊ ፔትሪ ታላስ " በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይቀልጣሉ ተብለው የሚጠበቁት በምስራቅ አፍሪካ የመጨረሻዎቹ የበረዶ ግግሮች በፍጥነት እየጠበቡ መምጣተቸው ... በምድር ስርዓት ላይ የማይቀየር ለውጥ ሊወጣ እንደሚችል አመላካች ናቸው" ብሏል፡፡
በአሁኑ ጥናቶች ላይ የተመረኮዘ ትንበያ መሰረት ሦስቱም የአፍሪካ ሞቃታማ የበረዶ ቦታዎች ማለትም የታንዛንያው ክሊማንጃሮ፣ የኬንያው ኬንያ ተራራ እና የኡጋንዳው ርዌንዞሪስ እንደፈረንጆቹ በ2040 ሊጠፉ ይችላሉ፡፡
በተጨማሪም "እንደፈረንጆቹ 2030 ቀድመው እርመጃዎች ካልተወሰዱ 118 ሚልዮን አፍሪካውያን ለአደጋ የሚጋለጡ ይሆናል ሲሉ" አበፍሪካ ህብረት የግብርና ኮሚሽነር ጆሴፋ ሳኮ ተናግሯል፡፡ እንደፈረንጆቹ 2020 1.2 ሚልዮን አፍሪካውያን በጎርፍ እና አውሎ ነፋሶች ምክንያት መፈናቀላቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡