የኮፕ28 ስብሰባ ለዓለም "ወሳኝ ምዕራፍ" መሆኑን ተመድ ገለጸ
ፍራንሲስ ለ78ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ቁርጠኛ በመሆን ጉባዔው መቻቻልን፣ አካታችነትን፣ ትብብርን እና ሰብአዊ ክብርን እንዲያንጸባርቅ አደርጋለሁ ብለዋል
በአረብ ኢምሬትስ የሚካሄደው የኮፕ28 ስብሰባ ለዓለም ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን የተመድ 78ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዝደንት ዴኒስ ተናገሩ
በአረብ ኢምሬትስ የሚካሄደው የኮፕ28 ስብሰባ ለዓለም ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን የተመድ 78ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዝደንት ዴኒስ ተናገሩ።
የጉባዔው ፕሬዝደንት ዴኒስ ፍራንሲስ በአረብ ኢምሬትስ የሚካሄደው ኮፕ28 ጉባዔ ዓለም ለፈጣን እና ለፍትሃዊ ስራ የሚነሳበት ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።
ፍራንሲስ ይህን ያሉት በአሜሪካ ኒው ዮርክ በተካሄደው 78ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ መክፈቻ ስነ ስርአት ላይ ነው። በጉባዔው መክፈቻ ላይ የ193 ሀገራት ድርጅቶች ተወካዮች መገኘታቸው ተገልጿል።
የጉባዔው ፕሬዝደንት ሆነው የመረጡት የትሪንዳድ እና ቶቤጎ ዜጋ የሆኑት ፍራንሲስ የጉባዔው ፕሬዝደንት ሆነው በሚሰሩበት ወቅት ስራቸውን በግልጸኝነት እና በኃላፊነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ፍራንሲስ ለ78ኛው የተመድ ጉባዔ ቁርጠኛ በመሆን ጠቅላላ ጉባዔው መቻቻልን፣ አካታችነትን፣ ትብብርን እና ሰብአዊ ክብርን እንዲያንጸባርቅ አደርጋለሁ ብለዋል።
ሰላም፣ ብልጽግና፣ መሻሻል እና ዘላቂ ልማት እንዲሁም በግጭት ውስጥ ላሉ ሀገራት የሚሆን መፍትሄ መሻት ፕሬዝደንቱ ትኩረት የሚያደርጉባቸው አራት ዋና ጉዳዮች ናቸው።
ፕሬዝደንቱ አባል ሀገራት በታደሽ ኃይል ላይ የሚያደርጉትን የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት እንዲጨምሩ እና ለአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል።
ፕሬዝደንቱ በዚህ ወር መጨረሻ የሚካሄደው የዘላቂ ሰላም ጉባዔ በሳንባነቀርሳ፣ በወረርሽኝ በመከላከል፣ በቅድመ ዝግጅት እና ምላሽ በመስጠት እና በጤና ሽፋን ጉዳይ አለምአቀፍ ትብብር ለመፍጠር ያስችላልም ብለዋል።
ጤናማ የሆነ ማህበረሰብ መገንባት የሰው ልጅን እና የመሬትን ህልውና ለማስቀጠል ጠቃሚ መሆኑን አስምረው ተናግረዋል ፕሬዝደንቱ።