በወታደርነት የሚመለመሉ ህጻናት ጉዳይ እንዳሳሰበው የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ በሶማሊያ (አሚሶም) አስታወቀ
በሶማሊያ ለውትድርና የህጻናት መመልመል በተመለከተም ከሰሞኑ በሞቃዲሾ ከሚመለከታቸው የሃገሪቱ መንግስት እና የህብረተሰብ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡
መማር ሲገባቸው በአሸባሪ ቡድኖች ተመልምለው በወታደርነት የሚሰማሩ ህጻናት ጉዳይ አሚሶምን ጨምሮ የሶማሊያ መንግስትን ስለማስጨነቁ በአሚሶም የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እና የስርዓተ ጾታ ጉዳይ ሃላፊ ካሪም አዴባዮ ህብረተሰቡ ህጻናትን ሊጠብቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ለጦርነት የሚመለመሉት ህጻናት ለሞት ከመጋለጥም በላይ ለተለያዩ የጉልበት ብዝበዛና ጾታዊ ጥቃቶች እየተጋለዩ መሆኑ በምክክር መድረኩ ተጠቁሟል፡፡
የሶማሊያ መንግስት የህጻናቱን ወታደራዊ ምልመላ ለማስቀረት እንደሚያስችል በማሰብ የተዘጋጀውን ፍኖተ ካርታ ፈርሞ ስለመቀበሉም ከአሚሶም የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡