በጀርመን በኤርትራውያን መካከል በተከሰተ ግጭት በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው ተገለጸ
የጀርመን ፖሊስ “26 አባላቶቼ ተጎድተዋል፤ ከእነዚህም 6 ፖሊሶች ሆስፒታል ገብተዋል” ብሏል
በጀርመን ስቱትጋርት ግጭት ላይ የተሳተፉ ከ200 በላይ ጥገኝነት ጠያቂ ኤርትራውያንን ማሰሩን ፖሊስ አስታውቋል
በጀርመን ስቱትጋርት ከተማ በኤርትራውያን ጥገኘነት ጠያቂዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካቶች መቁሰላቸውን የጀርምን ፖሎስ አስታወቀ።
የደቡብ ምዕራብ ጀርመኗ ስቱትጋርት ከተማ ፖሊስ በዛሬው እለት እንዳስታወቀው፤ በኤትርራ የባህል ፌስቲቫል ላይ በኤርትራውያን መካከል በተፈጠረ ግጭት 26 ፖሊሶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
በግጭቱ ከ26 ፖሊሶች በተጨማሪ በፌስቲቫሉ ላይ ሲሳተፉ ከነበሩ 4 ሰዎች፤ ፌስቲቫሊ ላይ አመጽ ካስነሱ መካከል ደግሞ ሁለት ሰዎች መጎዳታቸውን ነው ፖሊስ ያስታወቀው።
- በጀርመን በሚኖሩ ኤርትራዊያን መካከል ግጭት መከሰቱ ተገለጸ
- ጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁ “በግጭት ውስጥ የተሳተፉ የኤርትራ ስደተኞች በአስቸኳይ እንዲባረሩ እፈልጋለሁ” አሉ
ጉዳት ከደረሰባቸው ፖሊሶች መካከል 6 ፖሊሶች ክፉኛ ተጎድተው ሆስፒታል ገብተው ህክምና እየተከታተሉ መሆኑንም ነው ስቱትጋርት ከተማ ፖሊስ ያስታወቀው።
በጀርመን ስቱትጋርት ግጭት ላይ የተሳተፉ ከ228 በላይ ጥገኝነት ጠያቂ ኤርትራውያንን በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ መሆኑንም ፖሊስ ገልጿል።
በፌስቲቫሉ ላይ ምን ተፈጠረ?
ግጭቱ የተፈጠረው በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል ሲሆን፤ ይህም የኤርትራ መንግስት ደጋፊዎች ባዘጋጁት ፌስቲቫል ላይ ተቃዋሚዎች ተገኝው በመበጥበጣቸው ነው ግጭቴ የተቀሰቀሰው።
በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት ደጋፊዎች በተገኙነት የባህል ፌስቲቫል ላይ ቁጥራው እስከ 90 የሚደርሱ ኤርትራውያበን ጥገኝነት ጠያቂዎች ተገኝተው ነበር ያለው ፖሊስ፤ ሆኖም ግን በስፍራው ላይ ቀድሞ ተመደበው ነበሩ ተቃዋሚዎች በፌስቲቫሉ ተሳታፊ ላይ ብረት እና የተለያዩ ቁደሳቁሲችን መወርወር መጀመራቸውን አስታውቋል።
በጀርመን የሚኖሩ እርትራውያን በሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ በጊሰን ከተማ እርበእርስ ተጋጭተው 26 ፖሊሶች ተጎድተው እንደነበረ አይዘነጋም።
የኤርትራውያን ጥገኘነት ጠያቂዎች ከሳምንት በፊት በእስራኤል ቴልአቪቭ በተዘጋጀ የባህል ፌስቲቫል ላይ እር በእርስ በመደባደባቸው በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።
በተመሳሳይ በቅርቡ በስዊድን ስቶኮልም በተዘጋጀ የኤርትራዊያን በዓል ላይ ሁከት ተከስቶ ሰዎች መጎዳታቸው ይታወሳል።