ባለሙያዎቹ በኢራን የኑክሌር ጣቢያ ላይ በተመድ ተመድበው ቁጥጥር በማድረግ ላይ የነበሩ ናቸው
ኢራን በተመድ የተመደቡትን የኑክሌር ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች አባራለች።
በኢራን እርምጃ የተቆጣው ተመድ የሀገሪቱን ድርጊት በጹኑ አውግዞታል።
የአለምአቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ(አይኤኢኤ) ዳይሬክተር ጀነራል ራፋኤል ግሮሲ የኢራንን "ተገቢ ያልሆነ እና ያልተጠበቀ" የተመድ ባለሙያዎችን የማባረር እርምጃ አውግዘውታል።
ባለሙያዎቹ በኢራን የኑክሌር ጣቢያ ላይ በተመድ ተመድበው ቁጥጥር በማድረግ ላይ የነበሩ ናቸው።
ኢራን ይህን ውሳኔ የወሰነችው ምዕራባውያን ሀገሪቱ በድብቅ ዩራኒየም ማበልጸግ ጀምራለች የሚል ክስ ማሰማታቸውን ተከትሎ መሆኑን አርቲ ዘግቧል።
ኢራን ለአይኤኢኤ በርካታ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን ማባረሯን ማሳወቋን ግሮሲ በመግለጫቸው ተናግረዋል።
ባለሙያዎች ኢራን በፈረንጆቹ በ1970 የተፈረመውን ኑክሌር ያለማበልጸግ ስምምነት ማክበሯን ለመቆጣጠር የተመደቡ ናቸው።
ምንምእንኳን ስምምነቱ ኢራን የተቆጣጣሪ ባለሙያዎችን ፍቃድ መስረዝ የሚፈቅድላት ቢሆንም እርምጃው ያልተጠበቀ እና ተገቢ ያልሆነ ነው ብለዋል ግሮሲ።
የኑክሌር ጉዳይ ምዕራባውያንን ከኢራን ጋር አስርት አመታትን ላስቆጠረ አለመግባባት እና ፍጥጫ ዳርጓል።