የተመድ የጸጥታው ም/ቤት የማሊን የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ለማቆም ድምጽ ሊሰጥ ነው
13 ሽህ ወታደራዊ ኃይል ያለው ተልዕኮ ከሁለት ሳምንታት በፊት "ሳይዘገይ" እንዲለቅ ተጠይቋል
ማሊ በተልዕኮውና በማሊ ባለስልጣናት መካከል "የመተማመን ችግር" አለ ብላለች
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የጸጥታው ም/ቤት ላለፉት 10 ዓመታት በማሊ የዘለቀውን የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለማቋረጥ ድምጽ ሊሰጥ ነው።
የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ወታደራዊ መንግስት ከሁለት ሳምንታት በፊት 13 ሽህ ወታደራዊ ኃይል ያለው ተልዕኮ "ሳይዘገይ" እንዲለቅ ጠይቋል።
በ2021 ማሊ ከሩሲያው ዋግነር ቅጥረኛ ቡድን ጋር ትብብር ከጀመረች በኋላ፤ ሚኑሳ ተብሎ የሚጠራው የተመድ ተልዕኮ ጋር ውጥረት ውስጥ ገብታለች።
ለዓመታት የዘለቀው ውጥረት የሰላም ማስከበር የአየር እና የምድር ስራዎችን ለማቋረጥ የተገደደው የመንግስት እገዳ ተከትሎ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ሽህችን የገደለውን የእስልምና አማጽያን ለመከላከል ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል ተብሏል።
ተልዕኮው ሲነሳ የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ሊባባስ ይችላል ብለው የሰጉት አንዳንድ ባለሞያዎች፤ በቂ መሳሪያ ያልታጠቀው የማሊ ጦርና አንድ ሽህ ሚጠጉ የዋግነር ተዋጊዎች በሰሜንና በመሀል ላይ የሚገኙትን ግዛቶች የተቆጣጠሩ ታጣቂዎችን ይዋጋሉ።
የጸጥታው ም/ቤት ዲፕሎማት "ይህ የማሊ ውሳኔ ነው። እና እሱን ተግባራዊ ለማድረግ ቢያንስ አሰቃቂ ያልሆነውን መንገድ መፈለግ አለብን" ብለዋል።
የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አብዱላዬ ዲዮፕ በዚህ ወር ለጸጥታው ም/ቤት እንደተናገሩት በተልዕኮው እና በማሊ ባለስልጣናት መካከል "የመተማመን ችግር" አለ።