ተመድ በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ766ሺ በላይ ስደተኞችን ፍላጎት ለማሟላት ገንዘብ አጠረኝ አለ
ኢትዮጵያ ከኡጋንዳ ቀጥሎ ከፍተኛ ስደተኞችን እያስተናገደች ነው
ተመድ ለስደተኞቹ ከሚያስፈልገው 385 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 72 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ማግኘት ማግኘቱን ገልጿል
ተመድ ለስደተኞቹ ከሚያስፈልገው 385 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 72 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ማግኘት ማግኘቱን ገልጿል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ)የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እንዳጋጠመው አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ ለስደተኞች አስፈላጊ የሆኑ የምግብ፣የትምህርት፣ የጤናና የመጠለያ ፍላጎቶችን ለማሟላት ከሚያስፈልገው 385 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 72 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ማግኘት መቻሉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከፈረንጆቹ ሰኔ 30 ጀምሮ ኮሚሽኑ ከ766ሺ በላይ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በኢትዮጵያ በስተኞች ካምፕና በስድስት ክልሎች ይገኛሉ፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከኡጋንዳ ቀጥሎ በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ እያስተናገደች ትገኛለች፡፡
በኢትዮጵያ ያሉ ስደተኞች በአብዛኛው ከኤርትራ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከሶማሊያና ከሱዳን የመጡ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መንግስት መረጃን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ስደተኞችን በማስተናገድ የቆየ ልምድ ያላት ኢትዮጵያ በጎረቤት ሀገር በሚፈጠር ግጭትና ረሀብ ብዙዎች ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ፡፡
ኢትዮጵያ ከየመንና ከሶሪያ የመጡ ስደተኞችን ጭምር እያስተናገደች ትገኛለች፡፡