እስካሁን ከ3ሺ በላይ ስደተኞች በሊበያ ባህር ከመስጠም ተርፈዋል ተባለ
በአሁኑ ወቅት በሊቢያ 48,627 የተመዘገቡ ስደተኞችና ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዎች አሉ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን በተያዘው በፈረንጆቹ 2020 እስካሁን 3ሺ ሰዎች ከመስጠም ተርፈዋል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን በተያዘው በፈረንጆቹ 2020 እስካሁን 3ሺ ሰዎች ከመስጠም ተርፈዋል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን በዛሬው እለት እንዳስታወቀው በተያዘው የፈረንጆቹ 2020 እስካሁን 3000 ሰዎች በሊቢያ ባህር ከመስጠም መትረፍ መቻላቸውን አስታውቋዋል፡፡
አንደ የስደተኞች ኮሚሽን ከ3000ሺ በላይ ስደተኞች ወደ ባህር ከመስጠም ተርፈናል ብለው መመዝገባቸውን ሲጂቲኤን ድርጅቱን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
የስደተኞች ኮሚሽንና አለምአቀፍ የነፍስ አድን ቡድን በመተባበር ስደተኞች በሚደርሱበት ቦታ የመድሀኒትና ዋና ዋና እርዳታዎች እንደሚደረግ የስደተኞች ኮሚኒሽን አስታውቋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ እንደገለጸው በአሁኑ ወቅት በሊቢያ 48,627 የተመዘገቡ ስደተኞችና ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዎች አሉ፤ኤጀንሲው ለሚያከናውናቸው ተግባራትም 85 ሚሊዮን ዶላር ይፈልጋል፡፡
በፈረንጆቹ 2011 የሊቢያው መሪ ሙአማር ጋዳፊ ከስልጣን ከተነሱ በኋላ በነገሰው አለመረጋጋትና ትርምስ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ በአብዛኛው አፍሪካዊ የሆኑ ስደተኞች ከሊቢያ ተነስተው ሜዲትራኒያንን አቋርጠው ወደ አውሮፓ ይጓዛሉ፡፡
በሊቢያ የሚገኙ የስደተኛ መጠለያዎች ባህር ከመስጠም በዳኑ ወይንም በሊቢያ የጸጥታ ኋይሎች በተያዙ ስደተኞች የተሞሉ ናቸው፡፡