የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስጋቶች ዙሪያ የመጀመሪያ ስብሰባ ሊያደረግ ነው
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በዓለም ሰላህምና ደህንነት ላይ በሚያሳድረው ተጽዕኖ ዙሪያ ውይይት ይደረጋል

የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተቆጣጣሪ አካል እንዲቋቋም የቀረበውን ሀሳብ ደግፈዋል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስጋቶች ዙሪያ የመጀመሪያ ስብሰባ ሊያደርግ መሆኑ ተገለጸ።
ብሪታኒያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በዓለም ሰላህምና ደህንነት ላይ በሚያሳድረው ተጽዕኖ ዙሪያ ውይይት እንዲደረግ አጀንዳ ማስያዟን ተከትሎ ነው ስብሰባው የተጠራው።
በአለም ላይ ያሉ መንግስታት የአለምን ኤኮኖሚ ሊቀርፅ እና የአለም አቀፍ የፀጥታ ሁኔታን ሊለውጥ የሚችለውን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የደቀናቸው አደጋዎችን እንዴት መቀነስ እንደሚችሉ እያሰቡ ነው።
የጸጥታው ምክር ቤት የወሩ ፕሬዝዳት የሆነችው ብሪታኒያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቁጥጥር ዙሪያ ዓለም አቀፍ አመራ እንዲሰጥ ስታማትር ቆይታለች።
ብሪታኒያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በዓለም ሰላህምና ደህንነት ላይ በሚያሳድረው ተጽዕኖ ዙሪያ እንዲደረግ የጠራችው የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባም ነገ ይካሄዳል የተባለ ሲሆን፤ የብሪታኒየ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄምስ ክሌቨርሊ ስብሰባውን ይመራሉ ረብሏል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እንደ አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ያለ አለምአቀፍ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተቆጣጣሪ አካል እንዲቋቋም የቀረበውን ሀሳብ ደግፈዋል።