የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ያለበት ሁኔታ ምን ይመስላል? አስካሁን የምናውቀው
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 266 ፍሊስጤማውያን ጋዛ ውስጥ ተገድለዋል ተባለ
ሃማስ በካን ዮኒስ አቅራቢያ የእስራኤልን የመሬት ወረራ ማክሸፉን ተናግሯል
ከሁለት ሳምንት በፊት የፍልጤሙ ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተጀመረው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል።
በጦርነቱ እስራኤል በጋዛ የምትፈጽመውን የአየረ ድብደባ የቀጠለች ሲሆን፤ ሃማስም ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሱን እንደቀጠለ ነው።
የእስራኤል ሃማስ ጦርነት አዳሩን ምን ተፈጠረ?
እስራኤል በጋዛ የምትፈጽመውን የአየር ድብደባ የቀጠለች ሲሆን፤ አዳሩን ጃባሊያ ያስደተኞች ካምፕን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የአየር ድብደባዎችን አካሂዳለች።
የፍልስጠየም የቀይ ጨረቃ እስራኤል እያካሄደችው ባለው የአየር ድብደባ ሆስፒታሎች በአደጋኛ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ያለ ሲሆን፤ በተለይም አል ቁዱስ የተባለው ሆስፒታል በማንኛውም ሰዓት የቦምብ ድብደባ ሊደርስበት ይችላል ብሏል።
ሃማስ እስራኤል በካን ዮኒስ አቅራቢያ ልትፈጽም የነበረውን ወረራ ማክሸፉን ያስታወቀ ሲሆን፤ እስራኤልም በዚግንባር እንድ ወታደር እንደሞተባትና ሌሎች ሶስት ወታደሮቿ እንደቆሰሉ አስታውቃለች።
አሜሪካ ለእስራኤል ድጋፍን ለማጠናከር እና በመካከለኛው ምስራቅ ያላትን የመከላከያ ይዞታን ለማጠናከር ተጨማሪ ወታደሮችን ለመላክ ማቀዷን አስታውቃለች
ሰብዓዊ ድጋፍና ሞት
በራፋህ መሸጋገሪያ በኩል 17 የጭነት ተሽከርካሪዎች ወሳኝ የሆኑ ሰብዓዊ ድጋፎችን ወደ ዋጋ ማድረሳቸወ ታውቋል።
እስራኤል ባለፉት 24 ሰዓታት በጋዛ ባካሄደችው የአየር ድብደባም 266 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ 4 ሺህ 651 ፍልስጤማውያን ህይወት ያለፈ ሲሆን፤ ከ14 ሺህ በላይ ደግሞ ቆስለዋል።
የሃማስን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ የሞቱ እስራኤላውያን ቁጥር ከ1ን ብዛት ከ1 ሺህ 400 አልፏል።