በቀጠለው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት የተፈጠሩ አዳዲስ ነገሮች
የአየር ድብደባ ስታደርግ የቆየችው አስራኤል በእግረኛ ጦር ጥቃት ለመፈጸም ጋዛን በመክበብ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነች
የጋዛ ጤና ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በጋዛ ሆስፒታል ላይ በደረሰ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል
የጋዛ ጤና ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በጋዛ ሆስፒታል ላይ በደረሰ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።
በዚህ ጥቃት የእስራኤል እና የፍልስጤም ባለስልጣናት እርስ በእርስ እየተካሰሱ መሆናቸውን ሮይተረስ ዘግቧል።
ይህ ጥቃት በዌስትባንክ እና በመካከለኛው ምስራቅ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ ምክንያትም ሆኗል።
የሆስፒታል ጥቃት ጉዳይ
"መላው አለም ያውቀዋል። በጋዛ ያለውን ሆስፒታል ያጠቁት አረመኔ የሆኑት አሸባሪዎቾ እንጅ የእስራኤል መከላከያ አይደለም" ሲሉ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ተናግረዋል።
የእስላማዊ ጅሃድ ቃል አቀባይ ዳውድ ሸባብ በበኩሉ "ይህ ውሸት እና ፈጠራ ነው። ይህ ፍጹም ስህተት ነው፤ ለሚያደርጉት ወረራ ሽፋን እየሰጡ ነው" ብለዋል።
ዲፕሎማሲ እና ተቃውሞ
ጆርዳን ከፕሬዝደንት ባይደን፣ ከግብጽ እና ከፍልስጤም መሪዎች ጋር በጋዛ ጉዳይ በአማን ልታደርግ የነበረውን ስብሰባ መሰረዟን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አይመን ሳፋዲ አስታውቀዋል።
"በጋዛ በሚገኘው በአል አህሊ አረብ ሆስፒታል ፍንዳታ በጣም ተናድጃለሁ፤ ጥልቅ ሀዘንም ተሰምቶኛል" ያሉት ደግሞ ወደ እስራኤል እያቀኑ ያሉት ፕሬዝደንት ባይደን ናቸው።
በዚህ ዘግናኝ ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ መጽናናትን የተመኙት ባይደን አሜሪካ ንጹሃን እንዲጠበቁ የጸና አቋም አላት ብለዋል።
በሆስፒታሉ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት በአረቡ አለም ከፍተኛ ቁጣና ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል። ይህን ጥቃት ተከትሎ በፍልስጤሟ ራማላህ በፕሬዝደንት መሀሙድ አባስ ላይ የተነሳው ቁጣ ከቁጥጥር ውጭ በመውጣቱ
ፖሊስ ተቃዋሚዎችን በአስለቃሽ ጭስ በትኗል።
በኢራን የሚደረገፈው እና በእስራኤል ላይ ጥቃት የሰነዘረው ሄዝቦላም ሆስፒታሉ ላይ የደረሰውን ጥቃት አውግዟል።
የተመድ የጸጥታው ምክርቤት በእስራኤል እና ሀማስ ግጭት ተከትሎ በተፈጠረው የሰብአዊ ቀውስ ጉዳይ በብራዚል በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ድምጽ ይሰጣል ተብሏል።
ሀማስ በ50 አመታት ውስጥ ባደረሰባት ከባድ ጥቃት 1300 በላይ ዜጎቿን ያጣችው እስራኤል የእወሰደች ያለውን የአጸፋ ምላሽ አጠናክራ ቀጥላለች።
የአየር ድብደባ እያደረገች ያለችው አስራኤል በእግረኛ ጦር ጥቃት ለመፈጸም ጋዛን በመክበብ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነች።
የሰሜን ጋዛ ነዋሪዎች የእስራኤልን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ተሰድደዋል።