የዓለም ጤና ድርጅት፣ የአውሮፓ ህብረት ቱርክ፣ ኢራንና ኳታርን ጨምሮ በርካቶች ጥቃቱን እያወገዙ ነው
እስራኤል በጋዛ በሚገኘው ባፕቲስት ሆስፒታል ላይ ማምሻን የአየር ድብደባ ፈጽማለች።
እስራኤል በሆስፒታሉ ላይ በፈተጸመችው የአየር ድብደባ በትንሹ 500 መሞታቸው እና በርካታ ሰዎች መቁሰላቸው ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
እስራኤል በሆስፒታል ላይ የፈፀመቸውን ጥቃት ተከትሎ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ሀገራት ድርጊቱን እያወገዙ ይገኛሉ።
የአውሮፓ ካውንስል ፕሬዝዳንት በባፕቲስት ሆስፒታል ላይ የተፈጸመው ጥቃት ዓለም አቀፍ ህግን መጣስ ነው ሲሉ አውግዘዋል።
ኳታር እስራኤል ጦር ሆስፒታል መደብደብቡን ያወገዘች ሲሆን፤ ቱርክም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ባወጣችው መግለጫበጋዛ ባፕቲስት ሆስፒታል ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አውግዛለች።
የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በበኩላቸው፤ በጋዛ የሚገኘውን የባብቲስት ሆስፒታል ኢላማ መደረጉ እስራኤል መረሰታዊ የሰባዓዊነት ችግር እንዳለባት የሚያሳይ ምሳሌ ነው ብለዋል።
ኢራብ በበኩሏ እስራኤል በባፕቲስት ሆስፒታል ላይ የፈፀመችው ጥቃት “ጭካኔ የተሞላበት የጦር ወንጀል ነው” ብላለች።
የካናዳ ጠቀላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሬዱ፤ ከጋዛ የሚወጡ ዜናዎች አስደንጋጭ እና ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው፤ ሆስፒታል በቦምብ መምታት ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው ብለዋል።