ፖለቲካ
አሜሪካ የደህንነት መረጃ መነተፈ ያለችውን የ21 ዓመት ወጣት አሰረች
አፈትላኪ ሰነዶቹ አሜሪካ በአጋሮች ላይ የምታደርገውን ስለላና የዩክሬን ጦርነት አሳይቷል
ሁነቱ ዋሽንግተንን በዓለም አቀፍ ዙሪያ አሳፍሯል ተብሏል
የ21 ዓመቱ የአሜሪካ አየር ጥበቃ አባል ጃክ ዳግላስ ቴክሴራ አፈትልኮ በወጣው የደህንነት ሰነድ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ዋሽንግተንን በዓለም ዙሪያ "አሳፍሯል" በተባለው የሚስጥራዊ ሰነዶችን ምንተፋ የተጠረጠረውን ወጣት የአሜሪካ ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) በቁጥጥር ስር አውሏል።
ሰነዶቹ አሜሪካ በአጋሮች ላይ የምታደርገውን ስለላ እና የዩክሬንን ወታደራዊ ተጋላጭነቶችን በማሳየት ዋሽንግተንን አሳፍሮ ሰንብቷል።
የተመነተፈው የደህንነት መረጃ በፈረንጆች 2010 በዊኪሊክስ ድረ-ገጽ ላይ ከ700 ሽህ በላይ ሰነዶች፣ ምስሎች እና የዲፕሎማቲክ መልዕክቶች ከተለጠፈ በኋላ ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት እንደሆነ ታምኗል።
ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቴክሴራ "ያልተፈቀደ የብሄራዊ መከላከያ መረጃን ማስወገድ፣ ማቆየት እና ማስተላለፍ ከተባለው ምርመራ ጋር በተያያዘ በህግ ቁጥጥር ስር ውሏል" ሲል አሳውቋል።
የፍትህ ቢሮ በቴክሲራ ላይ ምን አይነት ክስ እንደሚመሰርት አልተናገረም ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ሆኖም ሆን ብሎ የሀገር መከላከያ መረጃዎችን በማቆየት እና በማስተላለፍ ወንጀል ሊከሰስ ይችላል መባሉን ዘገባው ጠቅሷል።