የአሜሪካ ችግሮች እንዲፈቱ እንጂ ለማንም የማዳላት ፍላጎት የላትም- ሰማንታ ፓወር
የዩኤስ ኤይድ ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል
ሳማንታ ፓወር ከጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ለመገናኘት ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስ ኤይድ) ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ከሰላም ሚኒሰትር ሙፈሪያት እና ከጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ ጋር መወያየታቸውን ገለጸዋል።
በውይይታቸውም በትግራይ ክልል ስላው ሁኔታ አንስተው መምከራቸውን አስታውቀዋል።
ሕወሃት እያደረገ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳሳሰባቸው የገለጹት ዋና አስተዳዳሪዋ፤ በሕወሃት ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአማራ ክልል 150 ሺህ ሰዎች በአፋር ደግሞ 76 ሺህ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ነው አረጋጠዋል።
በኢትዮጵያ ሁሉም ወገኖች ግጭትን እንዲያቆሙ የጠየቁ ሲሆን፤ ከግጭት ይልቅ ውይይት ማስቀደም አለባቸው ሲልም ተናረዋል።
ችግሮች ሁሉ መፈታት ያለባቸው በንግግር በመሆኑንና ይህንኑ ማስቀደም እንደሚገባ በማጥቀስ፤ የአሜሪካ መንግስት ችግሮች እንዲፈቱ እንጂ ለማንም የማዳላት ፍላጎት እንደሌላትም ተናግረዋል።
ዩኤስ ኤይድ ዋና አስተዳዳሪዋ ሳማንታ ፓወር ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ቆይታ በትግራይ ክልል ስላው ሰብአዊ ቀውስ ዙሪያ መምከራውንም በመግለጫቸው አንስተዋል።
በዚህም በክልሉ የሚቀርበው የሰብዓዊ ድጋፍ አሁንም መፋጠን እንዳለበት ጠቁመው በዚህም ከመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ጋር መግባባት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል።
ከቀናት በፊት የአሜሪካ መንግስት ለትግራይ ክልል 149 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ ማድረጉንም የገለጹት አስተዳሪዋ፤ ለኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እና ጤና ዘርፍ ተጨማሪ 45 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚሰጥም ጠቅሰዋል።
በጉብኝታቸው ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ለመገናኘት ቢያስቡም ከተማ ውስጥ የሉም መባላቸውን ገልጸዋል።
የዩኤስ ኤይድ ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ከሰሞኑ በምስራቅ አፍሪካ ጉብኝት በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።
በሱዳ የነበራውን ጉብኝት አስመልክቶ በትናትናው እለት በሰጡት መግለጫም ድጋፎችን ለሚፈልገው የትግራይ ህዝብ ማድረስ ካስፈለገ ሁሉም አካላት ግጭቶቹን ሊያቆሙ ይገባል ብለዋል።
ፓወር ለግጭቱ ወታደራዊ መፍትሔዎች እንደሌው በመግለጽም፤ አሜሪካ ህወሓት ኃይሎቹን በአስቸኳይ ከአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲያስወጣ ጥሪ ታቀርባለች ሲሉም ተናግረው ነበረ።