የአሜሪካ አየር ኃይል የውጊያ ዝግጁነት ማሽቆልቆሉ ጀርባ ያለው ሚስጥር ምንድን ነው?
የአሜሪካ አየር ኃይል የጦር ጄቶች የውጊያ ዝግጁነት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

የአየር ኃይሉ የውጊያ ዝግጁነት መጠን ዝቅተኛ የሆኖ ሲመዘገብ በ20 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው
የአሜሪካ አየር ኃይል የጦር አውሮፕላች የውጊያ ዝግጁነት በ20 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ ተዘገበ።
“ሚሊተሪ ዎች” የተባለው ጋዜጣ ይዞት እንደወጣው ሪፖርት ከሆን የአሜሪካ አየር ኃይል የውጊያ ዝግጁነት በ2024 አማካይ 67.15 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።
ይህም ከዚያ በፊት ከነበሩት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ የተመላከተ ሲሆን፤ ለአብነትም በ2023 አማካይ የዝግጁነት መጠን 69.92 በመቶ፤ እንዲሁም በ2022 ደግሞ 71.24 በመቶ አንደነበረም ሪፖርቱ አመላክቷል።
የአሜሪካ አየር ኃይል የውጊያ ዝግጁነት መውረድ ጀርባ ያለው ሚስጥር ምንድን ነው?
የጥገና ዋጋ
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ 5ኛ ትውልድ የሚባሉት እንደ "F-22" እና "F-35" ያሉ የውጊያ ጄቶች ለአሜሪካ አየር ኃይል የውጊያ ዝግጁነት ማሽቆልቆል ዋነኛ ምክንያቶች ተደርገው የሚጠቀሱ ሲሆን፤ ምክንያቱ ደግሞ ለጥገና ዋጋ ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቁ ነው ተብሏል።
የኤፍ 22 (F-22) የጦር ጄት የውጊያ ዝግጁነት ወደ 40.19 በመቶ አሽቆልቁሏል የተባለ ሲሆን፤ የኤፍ 35 (F-35A) የጦር ጄት የውጊያ ዝግጁነትም ቀድሞ ከነበረበት 55 በመቶ ወደ 51.5 በመቶ ዝቅ ማቱ ተነግሯል።
ለመጠገን በጣም ቀላል እና ዝቅተኛ ወጪ የይጠይቅ የነበረውን ኤፍ 16 (F-16) የጦር ጄት በኤፍ 35 (F-35) የጦር ጄት መተካቱ ለአየር ኃይሉ የውጊያ ዝግጁነት ማሽቆልቆል የበኩሉን ሚና እንደተጫወተም ሪፐርቱ አመላክቷል።
የምርት መዘግየት
የአሜሪካ አየር ኃይል የውጊያ ዝግጁነት እየተፈታተነ ያለው ሌላኛው ቸግር የውጊያ አውሮፕላች እና ፕሮግራሞች የምርት መዘግየት እንደሆነ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በተለይም እንደ "F-22" እና "F-35" ያሉ የውጊያ ጄቶች ላይ የታየው ተከታታይ የምርት መዘግየቶች ለአየር ኃይሉ የውጊያ ዝግጁነት መቀነስ ዋነኛ ሚና ተጫውቷል።
የኤፍ 22 (F-22) የጦር ጄት በብዘት እንዳይመረት የተከለከለ ሲሆን፤ ይህም አየር ኃይሉ በቀዝቃዛው ጦርት ወቅት ጥቅም ላይ እየዋሉ የነበሩ የጦር አውሮፕኖችን ከአገልግሎት ዘመናቸው ውጪ እዲጠቀም አስገድዶታል ነው የተባለው።
በኤፍ 22 (F-22) የጦር ጄት መተካት የነበረበት F-15C የጦር ጄት ከአገለግሎት ውጪ መሆን ሲገባው ከ20 ዓመታ በኋላ አሁንም አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፤ የ F-15C ጄት የውጊያ ዝግጁነትም 52.0 በመቶ ብቻ እንደሆነም ተነግሯል።
የአሜሪካ አየር ኃይል እምብዛም ጥቅም አልሰጠኝም ያለውን F-22 የጦር አውሮፕላን ምንም እንኳ የአገለግሎት ዘመኑ የሚያበቃበት ጊዜ ገና ቢሆንም ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ ከአገለግሎት ውጪ እንዲሆን እየጠየቀ ነው።
በአንጻሩ የውጊያ ዝግጁነት እጥረቱን ለማካካስ አዲስ የ F-15 የውጊያ ጄቶች ምርት ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱም ነው በሪፖርቱ የተመላከተው።