የሩሲያው “Su-25” የጦር ጄት ከአሜሪካው “A-10” የጦር ጄት ጋር ሲነጻፀሩ
ሁለቱም የጦር አውሮፕላች ለእግረኛ የውጊያ ክፍሎች የአየር ድጋፍ በመስጠት ረገድ ተቀናቃኞች ናቸው
ሁለቱም “በራሪ ታንኮች” ይባላሉ፤ ከሩሲያው “Su-25” እና ከአሜሪካው “A-10 ትክክለኛው "በራሪ ታንክ" የቱ ነው?
በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት አሜሪካ እና የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት የአሁኗ ሩሲያ በርካታ የተራቀቁ የጦር መሳሪያዎችን መፍጠር የቻሉ ሲሆን፤ በእነዚህ የጦር መሳሪያዎችም በጦረ ሜዳዎች ላይ ተቀናቃኞች መሆን ችለዋል።
ሩሲያ እና አሜሪካ “በራሪ ታንክ” የሚል ቅጽል ስም የተሰጣቸው የጦር አውሮፕላኖችን የታጠቁ ሲሆን፤ ስለ እነዚህ አውሮላኖች እንመለከታልን።
የሩሲያው “Su-25 ፍሮግፉት” የጦር ጄት እና የአሜሪካው “A-10 ዋርቶግ” የጦር ጄት ሁለቱም “በራሪ ታንክ” የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው ሲሆን፤ በመሬት ላይ በሚደረግ የዉጊያ ወቅት የአየር ድጋፍ በመስጠት ረገድ ተቀናቃኞች ናቸው።
ሁለቱም አውሮፕላኖች የተራቀቁ የጦር መሳሪያዎችን የታጠቁ ሲሆን፣ ዝቅተኛእና ከፍታ ስፍራዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር እንዲሁም የቦምብ ጥቃት መሰንዘር የሚችሉ ሲሆን፤ እግረኛ ወታደሮች የጠላት ጦርን እንዲያጠቁ ድጋፍ በመስጠት ይታወቃሉ።
የአሜሪካ “A-10 ዋርቶግ” የጦር ጄት
“A-10 ዋርቶግ” የጦር ጄት የተመረተው በፈረንጆቹ 1972 ሲሆን፤ አውሮፕኑ የተወለደው በአሜሪካ አየር ኃይል በምድር ውጊያ ላይ ያለውን ከፍተት ለመሙላት ታስቦ ነው።
“A-10 ዋርቶግ” የጦር ጄት ከአየር ላይ ወደ መሬት በሚደረጉ ውጊያዎች ወቅት “F-4 እና F-111” የተባሉ የአሜሪካ የጦር ጄቶችን ድክመቶች ሙሉ በሙሉ መሸፈን መቻሉም ይነገርለታል።
የሩሲያ “Su-25 ፍሮግፉት” የጦር ጄት
ሩሲያ “Su-25 ፍሮግፉት” የጦር ጄት በፈረንጆቹ 1978 ላይ ማምረት የመጀረች ሲሆን፤ የአውሮፕላኑ መመረት አላማም ከአሜሪካው “A-10” ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ይነገራል።
የሶቪየት አየር ሃይል ዝቅተኛ ከፍታ ያላቸው ስፍራዎች ላይ የውጊያ አቅሙ ጠንካራ የሆነ አውሮፕላን ማሰለፍ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው “Su-25 ፍሮግፉት” የጦር ጄት የተወለደው።
ከ “Su-25” በፊት “Su-17፣ Su-22፣ MiG-23BN እና MiG-27” የተባሉ የጦር ጄቶች ከአየር ላይ ወደ ምድር የሚደረጉ ውጊያዎችን ሲያግዙ ቆይተዋል።
የሩሲያ Su-25 እና እና የአሜሪካ A-10 በራ የጦር መሳሪያዎች ሲሆኑ፤ የምድር ኃይል ጠላቶች ላይ ስጋትን በማጫር የሚታወቁ ናቸው።
የአሜሪካው A-10 ዋናው ትጥቅ 30ሚሊ ሜትር መድፍሲሆን 1,174 ጥይቶች እንዳሉት ይነገራል፤ መድፉበደቂቃ እስከ 4,000 ዙሮች የሚደርስ እሳት የመትፋ ፍጥነት አለው ተብሏል።
የሩሲያ “Su-25ም ባለ 30 ሚሊ ሜትር ባለ ሁለት መድፍ የተገጠመለት ሲሆን፤ የሱ-25 ዋና መሳሪያዎች ሮኬቶች፣ ቦምቦች እና ከምድር ወደ አየር ሚሳኤሎች ናቸው።
Su-25 ትክክለኛ እና ኢላማዎችን የጠበቁ የቦብም ጥቃቶችን እንዲሁም በጨረር የሚመሩ ሚሳኤሎች ተጠቅሞ ጥቃት ከመፈጸም እጻር ጠንካራ ነው።
የሩሲያ Su-25 ለፍጥነት እና ለእንቅሰቃሴ ተመራጭ ሲሆን፤ የአሜሪካው A-10 ከፍ ያለ መሳሪያ ጭነት እንደሚበልጥ ይነገራል።