ዩክሬን ውጊያ ይቀይራል የተባለውን ኤፍ-16 የጦር ጄትን ልትረከብ ነው
እስካሁን ዴንማርክ፣ ዘ ኔዘርላንድስ፣ ኖርዌይ እና ቤልጄም ኤፍ-16 ጄቶችን ለዩክሬን ለማቅረብ ቃል የገቡ ሀገራት ሆነዋል
ዩክሬን በሩሲያ የተያዘባትን የአየር የበላይነት ለመቀልበስ አሜሪካ ሰራሽ የሆኑትን ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች ለሁለት አመታት ያህል ስትፈልግ ቆይታለች
ዩክሬን ውጊያ ይቀይራል የተባለውን ኤፍ-16 የጦር ጄትን ልትረከብ ነው።
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ያለውን ውጊይ ይቀይራል የተባለውን የመጀመሪያዋን ኤፍ-16 የጦር ጄት ከሰኔ እስከ ሐምሌ ባለው ጊዜ ውስጥ ከምዕራባውያን አጋሮቿ እንደምትረከብ ከፍተኛ የዩክሬን ወታደራዊ ባለስልጣን ተናግረዋል።
ዩክሬን በሩሲያ የተያዘባትን የአየር የበላይነት ለመቀልበስ አሜሪካ ሰራሽ የሆኑትን ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች ለሁለት አመታት ያህል ስትፈልግ እንደነበረ ሮይተርስ ዘግቧል።
እነዚህን ጄቶች ለዩክሬን ለመስጠት የተስማማችው የትኛዋ ሀገር እንደሆነች ዘገባው አልጠቀሰም።
እስካሁን ዴንማርክ፣ ዘ ኔዘርላንድስ፣ ኖርዌይ እና ቤልጄም ኤፍ-16 ጄቶችን ለዩክሬን ለማቅረብ ቃል የገቡ ሀገራት ሆነዋል።
የአየር ኃይል ቃል አቀባይ ኢልያ የቭላሽ እንደገለጹት የተወሰኑ የዩክሬን አብራሪዎች እነዚህን ጄቶች ለማብረር የሚያስችል ስልጠና አጠናቀዋል።
አብራሪዎቹ እና ግራውንድ ስታፍ ወይም የምድር ሰራተኞች የዩክሬን አጋር በሆኑት ምዕራባውያን ለወራት ሰልጥነዋል። የዩክሬን ጦር ከሩሲያ የሚቃጣባትን ጥቃት ለመመከት በሶቬት ህብረት ዘመን የተሰሩ እና የተወሰነ የሰው ኃይል የሚይዙ ጄቶችን ሲጠቀም ቆይቷል።
የሩሲያ ኃይሎች ቀስ እያሉ በዶንባስ ግዛት እየገፉ በመጡበት እና በሰሜን ምስራቅ ዩክሬን ካርኪቭ ከተማ አቅራቢያ ደግሞ አዲስ ግንባር በከፈቱበት ወቅት የጄቶቹ መምጣት የአየር ኃይል አቅማቸውን እንደሚያሳድግላቸው የዩክሬን ባለስልጣናት ተስፋ አድርገዋል።
የአሜሪካ የተወካዮች ምክርቤት በቅርቡ ለዩክሬን ወታድራዊ እርዳታ የሚውል የ61 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማጽደቁ ይታወሳል።
ዩክሬን ለሚደርስባት ሸንፈት የምዕራባውያን የጦር መሳሪያ ድጋፍ በፍጥነት አለመድረስን እንደ ምክንያት ስታቀርብ ቅይታለች።
ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን በከፊል የያዘቻቸውን አራት ግዛቶች ሙሉ በሙሉ እስከምትጠቀልል ድረስ ማጥቃቷን እንደምትቀጥል መግለጿ ይታወሳል።እስካሁን ዴንማርክ፣ ዘ ኔዘርላንድስ፣ ኖርዌይ እና ቤልጄም ኤፍ-16 ጄቶችን ለዩክሬን ለማቅረብ ቃል የገቡ ሀገራት ሆነዋል።