ቻይና በፔሎሲ ጉብኝት ምክንያት ከአሜሪካ ጋር የነበራትን ወታደራዊ ትብብር ማቋረጧን ማስታወቋ ይታወሳል
አሜሪካና እና ታይዋን ኢኮኖሚያዊ ትርገም ያለው ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል የንግድ ንግግር ለመጀመር ተስማምተዋል፡፡
አሜሪካ እና ታይዋን በትናንትናው እለት ያደረጉት ስምምነት አሜሪካ ለታይዋን ያላትን ተጨማሪ ድጋፍ ያሳያል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ሁለቱ ሀገራት ኤሜሪካ-ታይዋን የሚል የንግድ ማእቀፍ ይፋ ያደረጉ ሲሆን ይህም ቻይና በታይዋን ላይ ያላትን ተጽእኖ ለመከላከል ነው ተብሏል፡፡
የአሜሪካ የንግድ ተወካይ እንደገለጹት ሁለቱ ሀገራት በምን ጉዳይ መነጋገር እንዳለባቸው ተስማምተዋል፤የመጀመሪያው ዙር ንግግሮች በዚህ መኸር መጀመሪያ ላይ እንደሚደረጉ ይጠበቃል፡፡
የአሜሪካ የንግድ ተወከይ ሳራ ቢያንቺ "ፍትሃዊ፣ የበለጠ የበለጸገ እና ጠንካራ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያግዝ በድርድር ስልጣን ውስጥ አስራ አንድ የንግድ አካባቢዎችን” የሚሸፍኑ ጉዳዮች ላይ ንግግር ለማድረግ ማቀዳቸውን ገልጸዋል፡፡
አሜሪካ እና ታይዋን በንግድ ማመቻቸት፣በእቃ ቁጥጥር አሰራር እና በንግድ ላይ አግላይ የሆኑ እንቅፋቶችን በማስወገድ እና በመሳሳሉት ጠንካራ አጀንዳዎች ላይ ንግግር እንደሚያደርጉ ስለድርድሩ የወጣው ሰነድ ጠቅሷል፡፡
ሰነዱ እንደሚለው ከሆነ መደበኛ ንግግሩ የሚካሄድበት አላማ ሁለቱ አካላት ከፍተኛ ቁርጠኝነት እና ኢኮኖሚያዊ ትርጉም ያለው ውጤት ለማምጣት አላማ ያደረገ ነው፡፡ በሰነዱ ታይዋን አጥብቃ ስለምትፈልገው ነጻ የንግድ ልውውጥ ያለው ነገር የለም፡፡
ምንም እንኳን አሜሪካ ከታይዋን ጋር መደበኛ የሆነ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ባይኖራትም፣ ከታይዋን ጋር ያላት ግንኙነት የማጠናከር ፍላጎት አላት፡፡ አሜሪካ፣ ቻይና የግዛቷ አካል አድርጋ ከምታያት ታይዋን ጋር ያላትን ግንኙነት በቻይና ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ቻይና በቅርቡ የአሜሪካ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት ትንኮሳ ስትል ገለጸችው ሲሆን በፔሎሲ ላይ ማእቀብ መጣላ ይታወሳል፡፡
ቻይና በፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ምክንያት ከአሜሪካ ጋር የነበራትን ወታደራዊ ትብብር ማቋረጧን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡