የጋዛው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህም የሀገራቱ ወዳጅነት ተጠናክሮ ቀጥሏል
እስራኤል ከአሜሪካ በየአመቱ ከፍተኛውን ወታደራዊ ድጋፍ የምታገኝ ሀገር ናት።
ዋሽንግተን ለቴል አቪቭ በየአመቱ የ3 ቢሊየን ወታደራዊ ድጋፍ ታደርጋለች።
እስራኤል እንደ ሀገር ከተመሰረተችበት 1948 ጀምሮ ከአሜሪካ ወደ እስራኤል የተላከው ድጋፍም 330 ቢሊየን ዶላር መድረሱን የአናዶሉ መረጃ ያመለክታል። የጋዛው ጦርነቱም የሀገራቱ ጠንካራ ግንኙነት የተገለጠበት ነው
አሜሪካ በተመድ የጸጥታው ምክርቤት በጋዛ ዘላቂ ተኩስ አቁም ይደረስ ዘንድ የቀረቡ ሶስት የውሳኔ ሃሳቦችን ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ውድቅ አድርጋለች።
የጦር መርከቧን ወደ እስራኤል በማስጠጋትና የጦር መሳሪያዎችን በገፍ በመላክም ሃማስ ካልተደመሰሰ ጦርነቱ አይቆምም ላለችው ቴል አቪቭ ድጋፏን ማሳየቷን ቀጥላለች።
አሜሪካ ለ76 አመታት ሁነኛ አጋሯ ለሆነችው ቴል አቪቭ ያደረገችውን ድጋፍ በዝርዝር ይመልከቱ፦