አሜሪካ የአቬሽን ቴክሎጂዋን ለሩሲያ አሳልፎ በመስጠት የጠረጠረቻቸውን ባለሙያዎች አሰረች
በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የሩሲያ እና ምዕራባውያን ግንኚነት ሻክሯል
አሜሪካ እና ሌሎች ሀገራት በሩሲያን መከላከያ፣ ኤሮስፔስ እና የባህር ላይ ዘርፎች ያነጣጠሩ ቁጥጥር ሲያደርጉ ቆይተዋል
የአሜሪካን የኤክስፖርት ቁጥጥርን በመጣስ የአሜሪካን የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ወደ ሩሲያ ልከዋል በሚል በካንሳስ ከተማ ሁለት አሜሪካውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአሜሪካ የንግድ ዲፓርትመንት ባለስልጣን ማቲው አክስሌሮድ ተናግረዋል።
ከአመት በፊት ሩሲያ ዩክሬንን በወረረችበት ወቅት አሜሪካ እና ሌሎች ሀገራት በሩሲያን መከላከያ፣ ኤሮስፔስ እና ማሪታይም ዘርፎች ላይ ያነጣጠረ ቁጥጥር ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ሀገራቱ በሩሲያ መከላከያ፣ ኤርስፔስ፣ ማሪታይም፣ ሴክተር ላይ ሲደረግ የነበረው ቁጥጥር በሩሲያ ነዳጅ ማጣሪያ፣ ኢንዲስትሪ እና በንግድ ዘርፎች ላይ ሊስፋፋ ችሏል።
ሚስተር አክስልሮድ፣ የኤክስፖርት ማስፈጸሚያ የንግድ ረዳት ፀሃፊ፣ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአሜሪካ ጠበቆች ማህበር በማያሚ፣ ፍሎሪዳ በተካሄደ ዝግጅት ላይ ነው።
ስለታሰሩት ጉዳይ ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም ንግድ መምሪያው ከፌደራል የምርመራና ፍትህ መምሪያ አቃቤ ህግ ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ መክፈቷን ተከትሎ አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት በሩሲያ ላይ ማእቀብ ጥለዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ዘመቻውን የጀመረችው የምዕራባውያን ወታደራዊ ጥምረት የሆነው ኔቶ ወደ ቀድም የሶቬት ሀገራት እየተስፋፋ ነው፤ይህም ለደህንነቷ እንደሚያሰጋት በመግለጽ ነበር።
ጦርነቱ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ምዕራባውያንም ለዩክሬን መሳሪያ ማስታጠቃቸውን ቀጥለዋል።