“በራሪው” ቢ21 ሬይደር ስውር የኒውክሌር ቦምብ ጣይ አውሮፕላን
አሜሪካ ለዓመታት በሚስጥር የሰራችውን አዲሱን ቢ21 ሬይደር የጦር አውሮፕላን ይፋ አድርጋለች
የኒውክሌር አረር የመሸከም አቅም ያለው አውሮፕላኑ ያለ አብራሪ መጓዝ ይችላል
አሜሪካ ከሰሞኑ ለዓመታ በሚስጥር ስትገነባው የነበረውን “ቢ21 ሬይደር” የጦር አውሮፕላን ይፋ አድርጋለች።
ከፍተኛ ቴክኖሎጂ የተታጠቀው የጦር አውሮፓላኑ የኒውክሌር ቦምብ በመታጠቅ በስውር ጥቃቶችን መሰንዘር የሚችል መሆኑም ተነግሮለታል።
አዲሱ የጦር አውሮፕላን ከራዳር እይታ ውጪ መሆን ይችላል የተባለ ሲሆን፤ በስውር ጥቃት ፈጽሞ መመለስ እንደሚችልም ተነግሯል።
ቢ21 ሬይደር ስውር የኒውክሌር ቦምብ ጣይ አውሮፕላን በእብራ ወይም ያለ አብራ መጓዝ ይችላም ተብሏል።
አዲሱ ቢ21 ሬይደር ቦምብ ጣይ አውሮፕላን የአንዱ መሸጫ ዋጋ 700 ሚሊየን ነው የተባለ ሲሆን፤ የአሜሪካ አየር ኃይል ይህንን ዘመናዊ የጦር አውሮፕላን ለመታጠቅ ማዘዙመ ታውቋል።
አሁን ላይ የአሜሪካ አየር ኃይል 100 ቢ21 ሬይደር ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ለመግዛት ማዘዙም የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል።
የአዲሶቹ ቦምብ አውሮፕላኖች ይፋ የተደረጉት አሜሪካ፣ ከሩሲያ እና ቻይና ጋር በዩክሬን ጦርነት እና በታይዋን የግዛት አንድነት ጉዳይ ከፍተኛ የጂኦፖለቲካዊ ውጥረት በገባችበት ወቅት ነው።
የሩሲያ እና የቻይና ስትራቴጂክ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር ለማሳየት ረቡዕ እለት በፓስፊክ ውቅያኖስ አካባቢ ለስምንት ሰዓታት የፈጀ በረራ አድርገዋል።