የተለያዩ የጦር መሳሪያ የሚተኩሰው ሄሊኮፕተሩ በሰዓት 445 ኪ.ሜ ይበራል
አሜሪካ ካሏት የጦር ሄሊኮፕተሮች ውስጥ “አይበገሬው” የሚል መጠሪያ የተሰጠው “CV-22 ኦስፕሬይ” ሄሊኮፕተር አንዱ ነው።
ቦይንግ እና ሄል ሄሊኮፕተር ቴክስትሮን ኩባንያዎች በጥምረት ያመረቱት ሄሊኮፕተሩ በፈረንጆቹ በ2006 ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማራ ሲሆን፤ የተለያዩ ተልእኮዎችንም መፈጸም እንደቻለ ይነገርለታል።
ሄሊኮፕተሩ ከተሳተፈባቸው ዉጊያዎች ውስጥም ቀዳሚ እና ግዙፉ አሜሪካ በኢራቅ ያካሄደችው ዘመቻ እንደሆነም ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት።
በውጊያ ወቅት የጦር መሳሪያዎችን ለመተኮስ እና ወታደሮችን ለማጓጓዝ የሚውለው ሄሊኮፕተሩ፤ በአንድ ጊዜ ተቀምጠው ከሆነ 24 ወታደሮችን ቆመው ከሆነ ደግሞ 32 ወታደሮችን ጭኖ መጓዝ ይችላል ተብሏል።
CV-22 ኦስፕሬይ ሄሊኮፕተር ምን የተለየ ያደርገዋል?
ሮልስ ሮይስ አሊሰን AE1107C ሞተር የተገጠመለት ሄሊኮፕተሩ ለመነሳትም ይሁን ለማረፍ መደርደሪያ አያስፈልገውም የተባለ ሲሆን፤ ቀጥ ብሎ ወደላይ የሚነሳ እና ባለበት ተወዳች እየተምዘገዘገ ማረፍ ይችላል።
የረቀቁ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለት CV-22 ኦስፕሬይ ሄሊኮፕተር ዲጂታል ካርታ፣ ዲጂታል ሙሉ በሙሉ ዲጂታል የሆነ የአብራሪዎች ክፍል (ኮክፒት) እንዲሁም ራስን የመከላከል ስርዓቶች ተገጥመውለታል።
ሄሊኮፕተሩ ከባባድ ሮኬቶችን ጨምሮ ኒውክሌርን መቋቋም ይችላል የተባለ ሲሆን፤ “አይበገሬው” የተባለውም ከዚሁ በመነሳት ነው።
ሄሊኮፕተሩን ለማብረር ሁለት አብራሪዎች እና ሁለት የበረራ ኢንጂነሮች (መሃንዲሶች) የግድ ያስፈልጉታል ነው የተባለው።
CV-22 ኦስፕሬይ ሄሊኮፕተር በሰዓት 445 ኪሎ ሜትር የሚበር ሲሆን፤ በአንድ ጊዜ ነዳጅ ብቻ ከ925 ኪሎ ሜትሮች በላይ መብረር የሚችል ይችላል።
አየር ላይ ነዳጅ ከተሞላለት ደግሞ በየትኛውም የአየር ሁኔታ ውስጥ ከ3300 በላይ ኪሎ ሜትር ያለማቋረጥ መጓዝ እንደሚችል ተነግሯል።
ሄሊኮፕተሩ ላይ ወደላይ መተኮስን የሚያስችላቸው 7.62 ሚሊ ሜትር ሚኒገን ተገጠመለት ሲሆን፤ በመወጣጫው ላይ ደግሞ ካሊበር ማችን ገን ተገጥሞለተል።