በሱፐር ሶኒክ ፍጥነት የሚከንፈው ተዋጊ ጄቱ በሰዓት ከ2 ሺህ በላይ ኪ.ሜ ይበራል
ሩሲያ በቅርቡ ካሰማራቻቸው እና የበርካቶችን ቀለብ ከያዙ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ውስጥ “ሱኩሆይ ኤስዩ-57” የተባለው ተዋጊ ጄት አንዱ ነው።
“ሱኩሆይ ኤስዩ-57” የአምስተኛው ትውልድ ተዋጊ ጄት ሲሆን፤ ከድምጽ በበለጠ ፍጥነት የሚጓዝ ሱበርሶኒክ የጦር ጄት እንደሆነ ይነገራል።
ተዋጊ ጄቱ አርቴፊሻል ኢነተለጀነስ (ሰው ሰራሸ ክህሎት) ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ሲሆን፤ ይህም “ሱኩሆይ ኤስዩ-57” ከውጊያ በተጨማሪ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ አስችሎታል።
“ሱኩሆይ ኤስዩ-57” የጦር ጄት በአየር ላይ ውጊያ እንዲሁም ከአየር ወደ ምድር ለሚደረግ ዉጊያም ጥቅም ለይ የሚውል የጦር መሳሪያ ነው።
“ሱኩሆይ ኤስዩ- 57” ምን የተለየ ነገር ይዟል?
ባለ ሁለት ሞተር የሆነው “ሱኩሆይ ኤስዩ-57” የጦር ጄት በሶፐር ሶኒክ ፍጥነት የሚጓዝ ሲሆን፤ ይህም በሰዓት እስከ 2 ሺህ 100 ኪሎ ሜትር ድረስ እንዲከንፍ አስችሎታል።
በአንድ ተልእኮም እስክ 3 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር ማካለል የሚችል ሲሆን፤ በአየር ላይ ከ5 ሰዓት በላይ የመቆየት ብቃት እንዳለውም ይነገርለታል።
ከራዳር እይታ ውጪ በመሆን የፈለገውን ተልእኮ መፈጸም የሚችለው “ሱኩሆይ ኤስዩ-57” የጦር ጄት ከመሬት እስከ 20 ሺህ ሜትሮችን ከፍ ብሎ መበረርም ይችላል።
በውጊያ ወቅት የአየር በአየር ውጊያ፣ ከአየር ወደ ምድር ዉጊየሠን በብቃት መፈጸም የሚችል ሲሆን፤ ለሩሲያ ጦር ኃይል የመረጃ ማእከል በመሆን ያገለግላል።
ኤስዩ-57 ከሚታጠቃቸው ሚሳዔሎቹ ውስጥ 2 የአጭር እርቀት፣ ከሁለት የመካከለኛ ርቀት እንዲሁም 4 ሱፐርሶኒክ ሚሳዔሎች ተጠቃሽ ናቸው።