ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ለሶስተ ቀናት ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አዘዋል
በአሜሪካዋ ዋሺንግተን ካፒቶል ሂል በተሽከርካሪ በተፈጸመ ጥቃት በሁለት ፖሊሶች ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።
በዚህም ዊሊያም ኢቫንስ የተባለ የካፒቶል ፖሊስ አባል ህይወቱ ማለፉን ተነገረ ሲሆን፤ አንድ ፖሊስ ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱ ን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።
የካፒቶል ፖሊስ እንዳስታወቀው ጥቃቱን ኖህ ገሪን የተባለ የ25 ዓመት ወጣት የፈጸመው ሲሆን፤ ወጣቱ ሲያሽከረከር የነበረውን መኪና በፍጥነት እየነዳ ፖሊሶች ለፍተሻ ከከለሉት አጥር ጋር ማጋጨቱን አስታወቋል።
ወጣቱ በተሸከርካሪውአደጋውን ካደረሰ በኋላ ጩቤ ይዞ በመውረድ በስፍራው የነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት ማድረሱንም ፖሊስ ገልጿል።
ይህንን ተከትሎም በስፍራው የነበሩ ፖሊሶች ራሳቸውን ለመከላከል በወሰዱት እርምጃ ጥቃቱን ያደረሰው ወጣት መገደሉንም ነው የካፒቶል ፖሊስ ያስታወቀው።
በአሁኑ ወቅትም ኖህ ገሪን የተባለ የ25 ዓመት ወጣት ጥቃቱን እንዲፈጽም ምን አነሳሳው የሚለውን እያጣራ መሆኑን አስታውቋል።
በካፒቶል ሂል የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ከሶስተ ወራት በፊት መረበሻቻን ተከትሎ የተፈጸመው ጠቃት ከሽብርተኝነት ጋር ግንኙነት እንደሌለው የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የተሰማቸውን ሀዘን የገለጹ ሲሆን፤ በዋይት ሀውስ እና በሁሉም ፌደራል ተቋማት የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ለሶስተ ቀናት ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አዘዋል።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ መሸነፋቸውን ተከትሎ ስልጣናቸውን ለተመራጩ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ላለማስረከብ የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርጉ እነደነበር ይታወሳል።
ከነዚህ እንቅስቃሴዎች መካከል በነጩ ቤተመንግስት “ካፒቶል” ህንጻ የተፈጸመው ረብሻ አንዱ ነው፡፡
ጆ ባይደን በምርጫው ማሸነፋቸውን ተከትሎ ሲመክሩ የነበሩ የአገሪቱ የምክር ቤት አባላትን ሲረብሹ የነበሩት ጽንፈኛ የተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ደጋፊዎች ወደ ህንጻው በመግባት የተለያዩ ጥቃቶችን ፈጽመውም ነበር።