ቻይናና አሜሪካ ወደ ጦርነት ካመሩ ለዓለም ከባድ ውድመት እንደሚሆን ተገለጸ
ከአሜሪካ ጦር አዛዥ ጋር አልወያይም ያሉት የቻይና ጦር አዛዥ አሜሪካንን አስጠንቅቀዋል
የቻይና ባህር ሀይል የአሜሪካንን እና ካናዳን የጦር መርከብ ለመግጨት መሞከሩ ተገልጿል
ቤጂንግ እና ዋሸንግተን ወደ ጦርነት ካመሩ ለዓለም ከባድ ውድመት እንደሚሆበን ተገለጸ፡፡
በእስያ ከፍተኛ የወታደራዊ አመራሮች ጋር በተደረገው የጸጥታ እና ደህንነት ጉባኤ ላይ የአሜሪካ እና ቻይና ወታደሮች ጉዳይ ዋነኛው ትኩረት የሳበ አጀንዳ ነበር፡፤
ይእሜሪካ መከላከያ ዋና አዛዥ የሖኑት ሊዮልድ ኦስቲን ከቻይና አቻቸው ሊ ሻንግፉ ጋር መወያየት ቢፈልጉም ቤጂንግ ፈቃደኛ አለመሆኗ ይታወሳል፡፡
የቻይናው ጦር አዛዥ ሊ ሻንግፉ የአሜሪካ አቻቸውን ለማግኘት ፈቃደኛ ያልሆኑት በዋሸንግተረን ማዕቀብ ተጥሎብኛል በሚል እንደሆነ ተገልጿል፡፡
እኝህ የጦር መሪ ከአሜሪካ ጋር ስላለው ግንኙነት ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ በርካታ የዓለማችን ብዙሃን መገናኛዎች ጉዳዩን ዘግበዋል፡፡
እንደዘገባዎቹ ከሆነ ቻይና እና አሜሪካ ወደ ጦርነት የሚያመሩ ከሆነ በዓለም ላይ ከባድ ጉዳት ይደርሳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
አሜሪካ በእስያ ሀገራት እያደረገችው ያለው ጣልቃ ገብነት በአካባቢው ከባድ ውጥረት እና የጸጥታ ችግሮች እንዲከሰቱ ያደርጋሉ ሲሉም ጀነራል ሊ ተናግረዋል ተብሏል፡፡
በታይዋን ቀጠና ከሰሞኑ የቻይና ባህር ሀይል ንብረት የሆነ የጦር መርከብ የአሜሪካ አቻ መርከብን ከመግጨት ለጥቂት መትረፉ ተገልጿል፡፡
የቻይና የጦር መርከብ ከአሜሪካ በተጨማሪም የካናዳን ጦር መርከብ ለመግጨት ሞክሯል የተባለ ሲሆን የመርከቡ ካፒቴኖች ፍጥነትን ከመቀነስ ጀምሮ ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰዳቸው ግጭቱ እንዳይፈጠር አድርጓልም ተብሏል፡፡
የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ከቤጂንግ ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት ወደ ቤጂንግ አምርተዋል የተባለ ሲሆን ዲፕሎማቶቹ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በሚሻሻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡